“ቦንጋ በመልሶ መልማት ጎዳና”

Spread the love

ቦንጋ ከተማ በደቡባዊ ምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢ ከሚገኙ ከተሞች አንዷ ናት ፡፡ ከተማዋ በታሪክ ዕድሜ ጠገብ፣ ሀብተ ብዙና ተፈጥሮ አብዝቶ የቸረው ምድር ነው፡፡

ጥንታዊቷ ቦንጋ ከተማ የመካከለኛው ዘመን 1560ዎቹ ላይ የተቆረቆረች ከተማ ሲሆን በወቅቱም በአራት አቅጣጫዎች ከፍተኛ የሆነ የንግድ እንቅስቃሴ የነበረው የንግድ መናኸሪያ፣ የካፋ ነገስታት መኖሪያ እና መናገሻ ከተማ እንደነበረች ይነገርላታል፡፡

ተፈጥሮ አብዝቶ የቸረው ምድር ቢሆንም እንደ አንዳንድ የኢትዮጵያ ከተሞች በዕድሜ አንጋፋ በታሪክ ልክ ያለደገችና ለዚህም በዋናነት የሚጠቀሰው በየጊዜዉ የሚፈራረቀው አመራር እና የአስተዳደር ሥርዓት መሆኑ በሰፊው ይነጋራል፡፡

ቦንጋ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የፖለቲካ እና የአስተዳደር መቀመጫ ነው፡፡ ከተማዋ በዕድሜ ልክ አልዘመነችም በዚም ከከተማዋን ህብረተሰብ ፍላጎት ጋር የሚጣጣም አገልግሎት እየሰጠ አይደለም፡፡

ለዚህም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል እና የካፋ ዞን አስተዳደር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ከአካባቢው ተወላጆች ጋር በጋራ በመሆን ቦንጋ ከተማን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ለኢንቨስትመትም ተመራጭ ለማድረግ የከተማው መልሶ የመልማት ፕሮጀክት ተቀርፆ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል።

አካባቢው ሰፊ የመልማት እና የማደግ አቅም ያለው ቢሆንም ቀደም ሲል ለከተማዋ በቂ ትኩረት ሳይሰጥ በመቆየቱ እድገቷ መጓተቱን የቦንጋ ከተማ መልሶ ማልማት ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ አክሊሉ አበበ ገልፀዋል።

መኻል ከተማ ያለው ነባሩ ያረጀውና የቆየው ከተማ ለቦንጋ ከተማ ዕድገት ማናቆ ሆኗል፡፡ ይህንን ነባሩ መሃል ከተማ 44 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፈው፣ በሶስት ዙር የሚለማው እና በአምስት አመታት ለማጠናቀቅ የታቀደው የቦንጋ ብሔራዊ ሙዝዬም, የገበያ ስፍራ መልሶ ማልማት, የህዝብ አደባባዮች እንዲሁም መሰረተ ልማት ማሟላት ከተማውን መልሶ ለማልማት የትኩረት አቅጣጫዎች ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን የቦንጋ ከተማው መልሶ መልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አክሊሉ አበበ ተናግረዋል፡፡

ምቹ የሆነ መሰረተ ልማት የተሟላበትና ማራኪ የሆነ ከተማን መገንባትን አላማዉ ያደረገ የቦንጋ ከተማ መልሶ ማልማት ፕሮጀክት ህዳር ወር 2015 ዓ,ም ጀምሮ ትልቅ የፖለቲካ ትኩረት እና የባለሙያ ስብጥር በማካተት የራሱ የሆነ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ የተገባ መሆኑና በዚህም በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ይህ ፕሮጀክት ለካፋ ህዝብ ትልቅ ገጽታ ያለው ፕሮጀክት ነው ያሉት አቶ አክሊሉ መልሶ ማልማት ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ በህብረተሰቡ ተሳትፎ በሚሰበሰብ የሀብት ድጋፍ የሚሰራ ሲሆን በዚህም መላው የካፋ ዞን ህብረተሰብና ሌሎች ለልማቱ በጎ እይታ ያላቸው አካላት ጽኑ ፍላጎትና በሙሉ ተነሳሽነት ሀብት በማሰባሰብ ወደ ተግባር ተገብቶ ሥራው በጥሩ ደረጀ ላይ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡

የቦንጋ ከተማ መልሶ ማልማት ፕሮጀክት ለመተግበር 570 ሚሊየን በላይ በጀት ተይዞ ወደ ስራው መገባቱን አቶ አክሊሉ አበበ ገልጸው እስካሁን 136 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል ብለዋል፡፡

ለቦንጋ ከተማ መልሶ ማልማት ፕሮጀክት 269 ሚሊዬን 749 ሺህ 872 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ እስካሁን 136 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቦ ለዚሁ ልማት በተከፈተ ዝግ አካዉንት ዉስጥ መግባቱን ጠቅሰዋል፡፡

ለልማት ስራውም 28 ያረጁ መኖርያ ቤቶች፣ 30 የንግድ ተቋማት፣ 1 የሀይማኖት ተቋምና 2 የግል ትምህርት ቤቶች በማስነሳት በልማት ተነሺ ለሆኑ ማህበረሰብ ምትክ ቦታ እና የካሳ ክፍያ በመፈፀም ለልማት ዝግጁ በማድረግ ስራው በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።

ፕሮጀክቱ በአምስት አመታት ውስጥ በሶስት ዙር ተካፍሎ የሚለማ መሆኑንና በመጀመሪያ ዙር መልሶ ማልማት ፕሮጀክት ተግባራዊ የሚሆኑ ነበር የከተማ ቦታዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ የቡና ሙዝዬም 5.6 ሄክታር መሬት እና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቦንጋ ቅርንጫፍ ባስተጀርባ ያለው 1 ሄክታር የሚሆን የከተማ ክልል መሆኑን አቶ አክሊሉ አበበ ተናግረዋል፡፡

በዚህም አካባቢ ያሉ ነዋሪዎችን በማስነሳት ተገቢ የሆነ ምትክ መሬት እና የካሳ ክፍያቸውን በመፈፀም ለትላልቅ እንቨስትመንቶች እና የአከባቢው አልም ባለሀብቶች እንዲያለሙ ተሰጥቷል ብለዋል፡

ካፋ ቡና መገኛ ብቻ ሳይሆን በቡና ምርት ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት እንዲያስችል የኢትዮጵያ ብሔራዊ የቡና ሙዝዬም የበለጠ እንዲለማ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው የሙዝዬሙን ይዞታ ማስከበር ስራ በማጠናቀቅ ወደ 5.6 ሄክታር መሬት በዚሁ ሙዝዬም ስር በትልቅ ውበትና በጥሩ ደረጀ እንዲላማ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል፡፡

እስከአሁን በተሰራው የከተማው መልሶ መልማት ስራ ጥሩ ለውጥ አምጥተናል ያሉት አቶ አክሊሉ ካሳ ከፍለን ምትክቦታ ሰጥተን ሰዎችን በማስነሳት መሬቱን በሊዝ አስተላልፈን የወሰዱት አካላት ወደ ስራ እንዲገቡ የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በዚህም ልማታዊ ባለሀብቶች እንዲገቡ እና እንዲያለሙ በተሰራው ስራ ባንኮች፣ ኢንሹራንሶችና በርካታ ባለሀብቶች በከተማዋ መሬት ወስደው ግንባታ ለማከናወን ከፍተኛ ፍላጎት እያሳዩ ይገኛሉ ብለዋል።

የክልሉንና የከተማዋን የቱሪስት ፍሰት በመጨመር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከተማዋ የሚመጡ የቱሪስት ፍሰት በመጨመር የሆቴልና ቱርዝም ስራዎችን በፍጥነት በመስራት ረገድ ከፍተኛ የቦንጋ ከተማ መልሶ መልማት ስራ ከፍተኛ ሚና አለው፡፡

ለዚህም ከመጀመሪያው ጀምሮ የቱሪስት መዳረሻዎችን መልማትና የማስተዋወቅ ስራ ተቀዳሚ ተግባር በማድረግ ለቱርዝም ምቹና ሳቢ የሆነ ከተማ ለመፍጠር እያንደንዱ የፕላኑ ተግባራት በጥንቃቄና በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን አቶ አክሊሉ ገልፀዋል ፡፡

ይህንን መሠረት ያደረገ የመልሶ መልማት ሥራ የአካባቢውን ፀጋ በመለየት የተጀመረ ሲሆን በከተማው የተጀመረው ትላልቅ ሆቴሎች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁና አዳዲስ በሆቴልና ቱርዝም ዘርፍ ለመሰማራት የሚፈልጉ አካላትን ወደ ከተማዋ ለመሳብ ሥራዎች በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ አቶ አክሊሉ አበበ በመግለጫው አመልክተዋል፡፡

በአጠቃላይ ለፕሮጀክቱ ሲኬታማነት የማዘጋጃ ቤት ሚና ወሳኝ በመሆኑ ከመረጃ አቅርቦትና ከማስፈፀም አቅም ጀምሮ ሚናዉን በአግባቡ እየተወጣ እንደሚገኝም አንስተዋል፡፡

የቦንጋ ከተማ መልሶ መልማት ፕሮጀክቱ እዉቀት፣ ጉልበትና ግዜ እንዲሁም የህብረተሰቡን ተሳትፎና ድጋፍ የሚፈልግ በመሆኑ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ፕሮጀክቱ የከተማውን የዘመናት የመሰረተ ልማት ችግር የሚቀርፍ መሆኑን ተገንዝቦ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *