
ትውልዱ ላይ ሰላምን በመዝራት ረገድ እናቶች የማይተካ ሚና እንዳላቸው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
ኮሚሽኑ እናቶች ሰላም ወዳድ ማኀበረሰብ የመፍጠር አቅማቸውን በመጠቀም፤ በንግግር የሚያምን ትውልድ ለመፍጠር ይበልጥ እንዲሰሩም ጠይቋል፡፡
“በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት የእናቶች ሚና” በሚል ርዕስ የኮሚሽኑ የስርዓተ ጾታ እና አካታችነት አስተባባሪ አበባየሁ ደሳለኝ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡
“እናቶች በውይይት ያምናሉ” ያሉት አስተባባሪዋ፤ በምክክር ሒደቱ ውስጥ የእናቶች ተሳትፎ እንዲረጋገጥ ኮሚሽኑ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
የምክክሩን ጠቀሜታ በተለይም በወጣቶች አዕምሮ ውስጥ በማስረጽ ረገድ ሰፊ ስራ ከእናቶች እንደሚጠበቅም አመላክተዋል፡፡
እናቶች ያላቸውን ሰፊ ማኀበራዊ ትስስር በመጠቀም የሰላም ግንባታ ላይ ይበልጥ አንዲሰሩም አሳስበዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
