




የካፋ ዞን ጤና መምሪያ የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር መከላከያ ክትባት እና ልየታ ላይ ለባለድርሻ አካላት ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ ነው።
በጤናው ዘርፍ መንግስት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ ተናግረዋል።
እናቶች በማህፀን በር ካንሰር እንዳይሞቱና እንዳይጎዱ ቀድሞ በመለየት መከላከል እንደምገባ አስገንዝበዋል።
የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ ላይ እናቶች ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንዳለባቸው አቶ እንዳሻው ከበደ ጠቁመዋል።
በተለያዩ ኃይማኖትና ባህል ምክንያት በማድረግ የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ክትባት እና ህክምና እንዳይስተጓጎል ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን መወጣት እንዳለባቸው ዋና አስተዳዳሪው አሳስበዋል።
በሀገራች ብሎም በአለም አቀፍ ደረጃ የማህፀን በር ካንሰር ለህዝባችን የጤና እክል መሆኑን የካፋ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አክሊሉ አሰፋ ተናግረዋል።
ባለፉት 8 ወራት 5 ሺህ 8 መቶ እናቶች ተመርምሮ 83 እናቶች በማህፀን በር ካንሰር ምልክት መታየቱን ገልጸዋል።
ከነዚህ ውስጥ 43 እናቶች በአከባቢው ህክምና ያገኙ መሆናቸው ገልፀው የተቀሩ በከፍተኛ ህክምና ተቋማት ህክምና መውሰዳቸው እና እየወሰዱ መሆናቸው አመላክተዋል።
ከሁለት አመት ወዲህ በአመት ሁለት ጊዜ የሚደረግ ዘመቻ እንደ መደበኛ ክትባት ሆነው እንደሚቀጥል ኃላፊው አስረድተዋል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
