ሥራ አጥ ወጣቶችን በማህበረሰብ አገልግሎት በማሳተፍ ወደ ሥራ ሽግግር ማስገባት ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለጸ

Spread the love

ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ የኮሙኒኬሽን ፕሮግራም ማዕከል (JHUCCP) በወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራና በማህበራዊ አገልግሎት ወደ ስራ ማሸጋገር ላይ ፕሮጀክቱ በሚዛን አማን ከተማ ስልጠና ሰጥቷል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ እንዳሻው እንደገለፁት በሀገራችን ትኩረት ከተሰጣቸው ዘርፎች የስራ ዕድል ፈጠራ አንዱ መሆኑን ተናግረዋል።

የስራ ዕድል በመፍጠር መንግስት ፣የግል ተቋማት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የራሳቸው ድርሻ እንዳላቸው አቶ ተስፋዬ ገልጸዋል።

የስራ ዕድል መፍጠር ለሀገር ኢኮኖሚ ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ ሠላምና መረጋጋት ይፈጥራል ብለዋል።

ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ የኮምኒኬሽን ፕሮግራም ማዕከል (JHUCCP) በክልሉ በክልሉ 8 ሺህ ወጣቶችን በመመልመል ከነዚህም 200 የአሰልጣኝ ስልጠና በፕሮጀክቱ ወስደው ሌሎቹን አሰልጥነዋል ሲሉ አቶ ተስፋዬ ተናግረዋል።

ለወጣቶች የፍላጎት ስልጠና፣የክህሎት ስልጠና፣የቢዝነስ ፕላን ዝግጅት ስልጠና፣ በመስጠት የፋይናንስ ምንጭ የማመቻቸት ሥራ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የማህበረሰብ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ሂደቱን በሚገባ ለተወጡት በፍላጎታቸው ተደራጅተው ወደ ስራ የሚገቡበትን ፣ መቀጠር የሚፈልጉት ቅጥር እንዴት እንደሚያገኙ ፕሮጀክቱ እየሰራ መሆኑን የቢሮው ኃላፊ ተናግረዋል።

John hopkins university center for communication program (JHU CCP) የክልሉ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ እሌኒ ወርዶፋ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ በክልሉ ካሉ ዞኖች 13 ወረዳዎች ላይ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ ተገኝ ሽፈራው ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ የኮምኒኬሽን ፕሮግራም ማዕከል (JHUCCP) የክልሉ ደጋፊ እንደገለፁት በስራ አጥ ላይ ከመንግስት ጋር የጋራ ተልዕኮ በመያዝ ወጣቱ ማህበረሰቡን እያገለገሉ እይታን ማስተካከል ላይ ፕሮጀክቱ ይሰራል ብለዋል።

አሁን በፕሮጀክቱ ከታቀፊ ወረዳዎች የሚመለመሉ ሥራ አጥ ወጣቶች 70 ከመቶ ሴቶች 10 ከመቶ አካልጉዳተኞችን ያካተተ መሆን አለባቸው ሲሉ አቶ ተገኝ ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱ መደበኛ ሥራን የሚደግፍ ፕሮጀክት መሆኑን አቶ ተገኝ ጠቁመው አሁን በአዲስ የተካተቱ ወረዳዎችም የማህበረሰብ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የተመለመሉ ሥራ አጥ ወጣቶች በመስጠት ወደ ስራ የሚሸጋገሩበት ስራ የሚሰራ ፕሮጀክት መሆኑን መናገራቸዉን የቤንች ሸኮ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *