የቤንች ሸኮ ዞን የፓርቲና የመንግስት ሥራዎች አፈጻጸም ምልከታ ተደረገ

Spread the love

በክልሉ ምክትል ርዕሰመስተዳደርና የግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው የሚመራው ኢንስፔክሽን ቲም በቤንች ሸኮ ዞን ወቅታዊ የፓርቲና የመንግስት አጠቃላይ ተግባራት አፈጻጸም ተገምግሟል።

በክልሉ ምክትል ርዕሰመስተዳደርና የግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው እንደገለፁት የፓርቲውን እሳቤዎችና ፕሮግራሞች ከግቡ በማድረስ ለህዝቡ ተጠቃሚነት ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በቀጣይ በንቅናቄ የሚመሩት አጀንዳዎች የአረንጓዴ አሻራ፣የሌማት ትሩፋት፣የበልግ ፣ የኮሪደር ልማትና ሌሎች መሠል ተግባራት የሁሉም አጀንዳዎች በመሆናቸው ለተግባራዊነቱ በቀጣይ መትጋት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ጠንካራ ጎኖችን በማስጠበቅ በጉድለት የተነሱትን በቀጣይ የሥራ ግዚያት በመቅረፍ የተሻለ ለውጥ እንዲመጣ ጠንክሮ ሊሰራ ይገባልም ብለዋል።

የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን በበኩላቸው ዘላቂ ሰላምና ልማት እንዲመጣ ከመች ግዜውም በላይ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመው በቀጣይ የተቀመጡ አቅጣጫዎች ለተፈፃሚነታቸው ተረባርቦ መስራት ይጠበቃል ብለዋል።

በዞኑ እየተከናወኑ ባሉ የመሠረተ ልማት ስራዎች እየመጡ ያሉ ለውጦችን በሌሎችም በመድገም የህዝባችንን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

የቤንች ሸኮ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደግፌ ኩድን ወቅታዊ የፓርቲና የመንግስት የእስካሁን ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል።

በሪፖርቱም ላይ በዞኑ በልማትና መለወጥ ካም አስተዳደር እንዲ በፓርቲ ስራዎች ላይ ተመላክቷል።

በቀረቡት የፓርቲና የመንግስት ሥራዎች አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ሀሳብ በመስጠት ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት ውይይት ተደርጓል።

የህግ የበላይነትን ማስከበር ህገወጥ የነዳጅና የሌሎች ምርቶች ዋጋ ጭማሪ መከላከል ጋር በተያያዘ የአመራሩ ቁርጠኚነት ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍ ሊል እንደሚገባ ተነስቷል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *