48ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ መካሄድ ጀመረ

Spread the love

48ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

በስብሰባው የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐመድ አሊ ዩሱፍ፣ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስን (ዶ/ር) ጨምሮ የሕብረቱ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች፣ የሕብረቱ ተቋማት አመራሮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤቱ ዛሬና ነገ ለሁለት ቀናት በሚያደርገው ስብሰባ በተለያዩ አህጉራዊ አጀንዳዎች ላይ በጥልቀት ይመክራል።

ምክር ቤቱ በሚኖረው ቆይታ የካቲት 7 እና የካቲት 8 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚከናወነው 39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ የሚቀርቡ አጀንዳዎችን መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የዘንድሮው 39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ “ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽሕና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ይሆናል።

ይህ ስብሰባ አህጉራዊ ትብብርን ለማጠናከርና የአፍሪካን የጋራ ዕድገት ለማረጋገጥ ወሳኝ የሆኑ ውሳኔዎች የሚተላለፉበት መሆኑ ተመላክቷል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *