






የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፥ በኮንታ ዞን አመያ ከተማ በክልሉ መንግሥት የተገነባውን የአምራች ኢንዱስትሪ የማምረቻ ማዕከል መርቀዋል።
ፕሮጀክቱ በቀድሞው የደቡብ ክልል ጊዜ ተጀምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ግንባታው የተጓተተ ቢሆንም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምሥረታ ማግስት÷ የክልሉ መንግሥት ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቀው ለኅብረተሰቡ ተገቢውን አግልግሎት እንዲሰጡ በሰጠው ልዩ ትኩረት ተጠናቆ ለምርቃት መብቃት ተመላክቷል።
የማምረቻ ሼድ ግንባታው የክልሉ የልማት ድርጅት በኾነው ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን መከናወኑ የተገለጸ ሲሆን የማማከር ሥራው ደግሞ በክልሉ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የተከናወነ ሲሆን ፕሮጀክቱ ከ93 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መፍጀቱ ተገልጿል።
በምረቃው መርሐግብር የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው፣ የክልሉ ረዳት የመንግሥት ተጠሪ አቶ ነጋ አበራን ጨምሮ፣ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሀላፊዎች እና የአከባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
በዕድገቱ በዛብህ
