




ምክር ቤቱ በቅርቡ ላረፉት የምክር ቤት አባል የተከበሩ ሀጂ በድሩዘማን አብደላ ህልፈት የህልና ፀሎት በማድረግ ጉባኤ ተጀምሯል::
ምክር ቤቱ 4ኛ ዙር 12ኛ ዓመት 24ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ- ጉባኤ መርምሮ አፅድቋል።
የዞኑ ምክርቤት ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ግርማ ደፋር ለምክር ቤት አባላት የጉባኤ አጀንዳዎችን አቅርበዋል ።
በጉባኤው የምክር ቤት የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2018 በጀት ዓመት ትኩረት አቅጣጫዎችና በጀት ቀርበው እንደሚፀድቅ
የዞኑ አስፈፃሚ አካላት የ2017 ዓ.ም አፈፃፀም ሪፖርትና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ፣የከፍተኛ ፍርድ ቤት የ2017 ዓ.ም ሪፖርትና የ2018 በጀት አመት ዕቅድ እና የ2018 በጀት ዓመት የዞኑ የበጀት ረቅቅ አዋጅ ቀርቦ በምክር ቤቱ አባላት ውይይት ተደርገው እንደሚፀድቅ ይጠበቃል።
ከዞኑ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን የተገኘ መረጃ እንዳመለከተው በመደበኛ ጉባኤው የምክር ቤት አባላት የሴክተር መስሪያ ቤት የማናጅመንት አባላትና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛሉ ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
