ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፥ ከ280 በላይ አባወራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ አነስተኛ መስኖ መርቀው ከፍቱ።

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)÷ በዳውሮ ዞን፣ ማረቃ ወረዳ በክልሉ የመስኖ ኤጄንሲ የተሰራውን የውኒ አነስተኛ መስኖ መርቀው ከፍተዋል።

ከ144 ሄክታር የማልማት አቅም ያለው የመስኖ ፕሮጀክት የተገነባው ከ75 ሚሊዮን በሚጠጋ የክልል መንግሥት የበጀት ድጋፍ ነው።

ፕሮጀክቱ የ5.7 ኪሎሜትር ዋና የውሃ ካናል የመስመር ዝርጋታ እና ሌሎች የስትራክቸርና መካኒካል ሥራዎች ያካተተ ሲሆን ፕሮጀክቱ በዘላቂ የልማት ግቦች ማዕቀፍ መከናወኑ ተገልጿል።

የውኒ አነስተኛ መስኖ ከ280 በላይ አባወራዎችን ተጠቃሚ ማድረግ የሚችል አቅም ያለው መኾኑም ተገልጿል።

በምረቃ መርሐግብሩ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው፣ የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና የአከባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

በፕሮጀክቱ አጠቃላይ ሥራዎች ዙሪያ በክልሉ የመስኖ ኤጄንሲ ተቋም የሥራ ኃላፊዎች ገለጻ ተደርጓል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *