




የቤንች ሸኮ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ከEDI ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለዞን ሴክተር ተቋማት ለቡድን መሪዎች ለ3 ቀናት የሚቆይ የአቅም ግንባታ ስልጠና ዛሬ ተጀምሯል።
የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን ስልጠናውን በንግግር ሲከፍቱ እንደተናገሩት ለአንድ ሀገር ዕድገት የፐብሊክና ፋይናንስ ሴክተሮች ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።
በተለይም በእኛ ሀገር ተጨባጭ ሁኔታ ህብረተሰቡ አብዛኛውን አገልግሎቶች ከመንግስት ተቋማት የሚያገኝ በመሆኑ የፐብሊክ ሰርቫንቱን አቅም ማሳደግና የአገልጋይነት መንፈስን መላበስ ያስፈልጋል ያሉት አቶ ሀብታሙ ያለንን የተፈጥሮ ሀብትና ጸጋ ወደ ገንዘብ ቀይሮ ለመጠቀም አሰራራችንን ማዘመን ይገባል ብለዋል።
የህዝቡ ልማትና ዕድገት ድምር ውጤት የሀገር ዕድገት ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ፐብሊክ ሰርቫንቱ በአመለካከት ፣ በተግባር እና በክህሎት ብቁ ማድረግ ይገባል ብለዋል ዋና አስተዳዳሪ።
የቤንች ሸኮ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ግዛው ኃይሌ እንደተናገሩት ጊዜውን የዋጀ ፐብሊክ ሰርቪስና ፐብሊክ ሰርቫንት ለመፍጠር እየተሰራ ነው ብለዋል። በአመለካከት ፣ በተግባር ፣ ብቃትና ተነሳሺነት ያለው ኃይል ለመገንባት በየጊዜው የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል።
ብቃት ፣ ጥራትና ተገቢውን አገልግሎት ለህዝብ መስጠት እንደ ሀገር ከተያዙ የሪፎርም አካል አንዱ መሆኑን የተናገሩት አቶ ግዛው ፈጣን አገልግሎትን ለህዝቡ ተደራሽ ለማድረግ ፣ የስራ ላይ ተነሳሽነትን ለመጨመር ፣ አማራጮችን ለማስፋትና በውጤት ለማጀብ ያለመ ስልጠና ለ3 ተከታታይ ቀናት ይሰጣል ብለዋል።
እንደ ዞን ከ13ሺ በላይ ፐብሊክ ሰርቫንቶች በስራ ላይ ይገኛሉ ያሉት አቶ ግዛው በቀጣይም በተዋረድ ለሰራተኛውና ለአመራሩ ስልጠናው እንደሚሰጥ ገልጸዋል።
በመድረኩ በዞን ማዕከል ከሚገኙ 20 ተቋማት የማኔጅመንት አካላት በ3 ቡድን ተከፋፍለው ስልጠናውን እየወሰዱ የሚገኙ ሲሆን ከEnterprenership Development Institute (EDI) ኢትዮጵያ የመጡ አሰልጣኞች ስልጠናውን እየሰጡ ይገኛሉ።
