




በምዕራብ ኦሞ ዞን ግብርና አካባቢ ጥበቃ ህብረት ሥራ መምሪያ የ2017ዓ/ም የበጋ ስንዴ ልማት አፈጻጸምና የ2018ዓ/ም ዕቅድ ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የተገኙት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ታምሩ ቦኒ እንደገለጽት በሀገራችን ከዝናብ ጥገኝነት የተላቀ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በማከናወናችንና ከተረጂነት በመላቀቃችን የተነሳ የሀገር ክብርና ሉዓላዊነትን አረጋግጠናል ሲሉ ተናግረዋል ።
የስንዴ ልማት በሀገራችን ማልማት ኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን ፖሊቲካ ጭምር በመሆኑ በትኩረት እንድሰራ ዋና አስተዳዳሪ አሳስበዋል።
የምዕራብ ኦሞ ዞን ግብርና አካባቢ ጥበቃና ህብረት ሥራ መምሪያ ኃላፊ አቶ መልኬ ኬላጌ በበኩላቸው በዞኑ በ2017ዓ/ም የነበረው የመደበኛና የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ዕቅድ 1700ሄ/ር ለማከናወን የታቀደ ሲሆን አፈጻጸሙ 492 ሄ/ር ብቻ በመሆኑ አሁን ትኩረት ተደርጎ እንደሚሠራ ተናግረዋል ።
በዞኑ በ2018ዓም በበጋ መስኖ በሆልቲካልቸር ላይ ሀቅሞቻችንን ለይተን ምርታማነትን ለማረጋገጥ 1000ሄ/ር መሬት ይታረሳል ብለዋል ።
ለውይይት ሰነድ እየቀረበ ሲሆን በመድረኩም የሚመለከታቸው የዞንና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
