የህዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ቀዳሚ ትኩረት መሆኑ ተገለጸ

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ የህዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥን ማዕከል ያደረገ የክልልና የዞን ምክር ቤቶች የ2018 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ግምገማ በታርጫ ከተማ ተጀመረ።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ፣ የምክር ቤት አባላት በየደረጃው የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከምንጊዜውም በላይ በትጋት እንዲሰሩ አሳስበዋል።

“በሩብ ዓመቱ የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠልና የታዩ ድክመቶችን በማረም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል ሲል የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል።

በዚህ ወሳኝ መድረክ ላይ ከሁሉም ዞኖች የተውጣጡ ዋናና ምክትል አፈ ጉባኤዎች፣ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በመሳተፍ ላይ ሲሆኑ፣ ግምገማው በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *