የጤናው ዘርፍ ለሀገር እድገት ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ

Spread the love

በምዕራብ ኦሞ ዞን “የጤናው ዘርፍ አርበኝነት ለሀገር ዕድገት ዞናዊ የጤና ባለሙያዎች የዉይይት መድረክ ተደርጓል።

በመድረኩ የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ በድሉ መዓዛ እንደተናገሩት ሀገራችን እያደረገ ያለው የብልጽግና ጉዞ የጤና ባለሙያዎች የበኩላቸውን ሃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

ለበርካታ ሰዎች ከልጅነታቸው የሚመኙት የጤና ባለሙያነት ከፈጣሪ በታች ወድ የሆነ የሰው ህይወት በእናተ እጅ ከመሆኑም ጋር ተያይዞ በታታሪነት ማገልገል እንደሚገባ ተናግሯል።

የዜጎች ጤና ለመጠበቅ ጤናን በማበልጸግ በሽታን በመከላከል አክሞ በማዳን ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆናቸው አክሎበታል።

የዞኑ ጤና መምሪያ ሃላፊ አቶ ሼማጂ ጉሪጭማ በበኩላቸው የጤና ባለሙያዎች አርበኝነት ለሀገር እድገት ላይ ሚናቸውን ከፍተኛ መሆኑ ገልጸዋል።

የሀገር ብልጽግና ማሳከት የሚቻለው በአካል የጠነከረ እና በአእምሮ የበለጸገ ማህበረሰብ ሲኖር ነው ብልዋል።

የጤና ዘርፍ ዉጤታማ የሚሆነው የማህበረሰብ ተሳትፎ ፤የአጋር ተቋማት ፤የግል ጤና ተቋማት እና የሌሎች ዘርፎች ተሳትፎ ሲኖር ከመሆኑም አንጻር ተቀናጅተው መሰራት ይጠበቃል ነው ያሉት።

በጤና ዘርፍ የመንግስት አቅጣጫዎች እና የቀጣይ ዕቅዶች ላይ በሰነድ ቀርበው ሰፊ ዉይይት ተደርጓል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *