በክልሉ የመንግሥት የልማት ሥራዎችን የሚያደናቅፉ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችን በተቀናጀ መንገድ መፍታት ያስፈልጋል፦ርዕሰ መስተዳድር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የአስተዳደር ዘርፍ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት ባለፉት የ9ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሸ ዋጌሾ በተገኙበት ተገምግሟል።

በዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረኩ በክልሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በአስተዳደር ዘርፍ ተቋማት ታቅደው በጥንካሬ የተከናወኑ ተግባራት እንዲጠናከር፣ በክፍተት የታዩትን በመገምገም እና ቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ ሀሳብ አስተያየት ተነስተው በጥልቀት ውይይት ተደርጓል።

በዚህም የክልሉ ርዕሰ መስተደድር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በክልሉ በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በሀብት ብክነት፣ ከልማት ሥራዎች ውጤታማነት ችግር ጋር ሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችን በተቀናጀ መልኩ መፍታት እንደሚገባ ገልጸዋል።

በክልሉ በሁሉም ተቋማት በየጊዜው የሚከናወኑ ተግባራት ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻሎች እየታዩ ተቋማትን የሚያሻግሩ እና የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት በመከናወን ላይ መሆናቸውን አንስተዋል።

የክልሉን ሠላምና ፀጥታን ለማረጋገጥ እየተከናወኑ የሚገኙ ሥራዎች መጠናከር እንደሚገባቸውም ርዕሰ መስተዳድሩ አንስተዋል።

ክልላዊ የፀጥታ መዋቅሮችን ከማጠናከር አኳያ የሚሊሻ አባላትን ማሰልጠን፣ ህዝቡን በማስተባበርና ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመቀናጀት የሥጋት ቀጠናዎችን መለየት፣ እርስ በእርስ ግዲያዎችና ዝርፊያዎችን ማስቆም እንዲሁም ህገወጥ ጦር መሳሪያ ምዝገባ በትኩረት ሊሰራ ይገባልም ብለዋል።

ህገወጥ ንግድና ኮንትሮባንድ መከላከል እንዲቻል የክልሉ ፀጥታ ተቋማት ከንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ጋር በቅንጅት እንዳሰሩ አሳስበው በወንጀል መከላከል እንዲሁም በማረሚያ ተቋማት ቅሬታ አሰጣጥ ጉዳዮች በጥንቃቄ እንዲመሩ ጠቁመዋል።

ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ሙስና እና ብልሹ አሠራሮችን መከላከል ሥራ ላይም ከህዝቡ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በመቀበል የሚባክኑ የመንግስት በጀት ማዳንና አልፎ ሲገኝ እርምት እርምጃ መውሰድና ህግን የማስከበር ሥራ ሥራ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።

የባህል ፍርድ ቤቶች ማጠናከርና ዉጤታማ ማድረግ፣የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድም መምራት እንደሚገባ አንስተዋል።

በክልሉ በመንግሥት ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶች ቀልጣፋና ውጤታማ እንዲሆን በቴክኖሎጂ ማስደገፍ ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የፐብሊክ ሠርቪስ መረጃ ማጥራት፣ፐብሊክ ሠርቫንቱ የመንግስት የሥራ ሰዓት በማክበር ህዝብን ከማገልገል አንጻር ጠንካራ የአሰራር ሥርዓት ሊዘረጋ ይገባል ነው ያሉት።

በክልሉ መንግስት ኮሙኬሽን ቢሮ ወቅታዊ እና ሚዛናዊነቱን የጠበቀ መረጃዎችን ተደራሽ ከማድረግ አንጻር እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች መጠናከር እንደሚገባቸው ተናግረው የክልሉ የሚዲያ ኔትወርክ ማደራጀት ሥራ ከግብ እንዲደርስ እና ሚዲያ ሞኒተሪንግ ሥራ በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በማከልም በክልሉ የመንግሥት የልማት ሥራዎችን የሚያደናቅፉ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችን በተቀናጀ መልኩ መፍታት እንደሚጠበቅ ገልጸው ከታች የሚመጡ የህዝብ ቅሬታ ማዳመጥና ምላሽ መስጠትና የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትኩረትእንዲደረግ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *