



ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት አምስት ዓመታት በሁሉም ዘርፎች አበረታች ውጤቶችን ማስመዝገብ መቻሉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ተሳታፊዎች ገለጹ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት “የሀሳብ ልዕልና ለሁለተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሀሳብ የፓርቲውን 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በፓናል ውይይትና በተለያዩ መርሃ ግብር ተከብሯል።
በመርሃ-ግብሩ ተሳታፊዎች ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት አምስት ዓመታት በክልሉ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች አበረታች ውጤቶችን ማስመዝገብ መቻሉን ገልፀዋል ።
ከተሳታፊዎች መካከል የኮንታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ታስፉ ባለፉት አምስት አመታት ብልጽግና ፓርቲ እንደ ሀገርና በክልላችን ያመጣቸው ለውጦች እና ጉድለቶች ምን እንደሚመስል በዚህም በክልል ደረጀ ውይይት እየተደረገ መሆኑን አንስተው ዛሬ ላይ በሁሉም ዘርፍ ልባል በሚችል መልኩ የተሻለ ሀገር መገንባት የሚያስችል መንገድ ውስጥ እንገኛለን ብለዋል፡፡
ሀገራዊ ጉዞአችን በብዙ መልኩ መልካም እምርታ ያለበት፣ ትልቅ ለውጥ ማስመዝገብ የታቸለበት እና በህዝብ ዘንድ እንደችግር ይነሱ የነበሩ ጉዳዮችን በየደረጃው እየፈታ የመጣ ፓርቲ መሆኑንም በንግግራቸው አጋርተዋል፡፡
በዚህም ከመጡ ለውጦች አኳያ እንደ ኮንታ ዞን ስንመለከትም የዛሬ ሶስት ዓመት በዞን የመደራጀት ዕድል ያገኘበት ለዞናችን ትልቁ የብልጽግና ትሩፋት ተብሎ የሚወሰደው ተግባር መሆኑን ለረዥም አመታት በኮንታ ህዝብ ዘንድ ይነሳ የነበረው ጥያቄ ምላሽ ያገኘበት እንደሆነም አቶ ታከለ ታስፉ አብራርተዋል፡፡
ሌላኛው ተሳታፊ ወጣት የማታወርቅ ደምሴ ከቦንጋ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ የተናገረውን ወደ መሬት የሚያወርድ ፓርቲ መሆኑን ያነሳ ሲሆን በሁሉም ዘርፍ እጅግ የሚያኮራ ተግባራትን እያከናወነ ማምጣቱንም ተናግረዋል፡፡
በቦንጋ ከተማ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ፣ የአየር ማረፊያ ግንባታ እና በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽ/ቤት የተገነባው የቦንጋ ከተማ ዳቦና ዱቄት ፋብርካ ተመርቆ ለከተማው ማህበረሰብ አገልግሎት እየሰጣ መሆኑንና ይህም ኑሮ ውድነቱን እፎይ የሚያስብልና አንዱ የብልጽግና ፓርቲ ቱሩፋቶች መሆኑን ገልጿል፡፡
የክልሉ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ባለሙያ ወ/ሮ ሰላማዊት ኃይሉ በበኩሏ የብልጽግና ፓርቲውን 5ኛ ዓመት ጉዞ ላይ በግብርናና በመንገድ መሠረተ ልማት ዘርፍ በርካታ የሕዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
ፓርቲው በቀጣይ ያሉባትን ውስንናቶች ለመቅረፍ ከህብረተሰቡ ጋር በመመካከርና በሚነሱ ሀሳቦች ላይ የጋራ ውይይት በማድረግና አሁን የመጡ ለውጦችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደለበትም አንስተዋላች፡፡
ወ/ሮ ሰላማዊት ኃይሉ አክላም ፓርቲው በዚህ 5 አመት ውስጥ ከሴቶች ተጠቃሚነት አንፃር ጥሩ ተግባር መከናወን መቻሉንና በቀጣይም ሴቷ በልማት ጠንክራ እንድትሄድ ከማድረግ አንፃር በቀጣይ አጠናክሮ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋላች፡፡
ሌላኛዋ ከቦንጋ ከተማ የመድረኩ ተሳታፊ ወ/ሮ አስቴር መኩሪያ ብልጽግና ፓርቲ በአጠቃላይ በአምስት አመታት ውስጥ በማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና በፖሊስ ዘርፎች ጥሩ እምርታዊ ለውጥ ማምጣት የሚያስችሉ በርካታ ተግባራት መከናወኑን ተናግረው በቀጣይ በተለይም ሠላም ለሁሉም ነገሮች መሠረት በመሆኑ በሀገራችን በአንድ አንድ አካባቢዎች የሚታዩ የሠላም እጦት እልባት እንዲያገኝና ህብረተሰቡ በሠላም ወጥቶ እንዲገባና ሠላማዊ ኑሮ እንዲኖር በሠላምና ፀጥታ ዘርፍ ትኩረት አድርጎ መስራት ይጠበቃል ብለዋል፡፡
በተከተል ወ/ሚካኤል
