የብልፅግና ፓርቲ የከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ተጀመረ!

Spread the love

ስልጠናው ”ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሀሳብ ለብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የተዘጋጀ የመጀመሪያ ዙር ስልጠና በዛሬው ዕለት በአዳማ ከተማ ተጀምሯል።

በስልጠናው ላይ ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉ ነው።

የስልጠናው አላማ አመራሮች ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን ተገንዝበው፣ ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር፣ ፓርቲው ለህዝቡ የገባውን ቃል ማስፈፀም የሚያስችል የአመራር አቅም እንዲፈጥር ያለመ መሆኑን የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ገልጸዋል።

ፓርቲው ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በሚያደርገው ትግል የአመራሩ የአስተሳሰብ እና የተግባር አንድነት ወሳኝ መሆኑን በጽኑ እንደሚያምንና በየደረጃው ያሉ አመራሮችን በስልጠና አቅም የመገንባት ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አቶ አደም ተናግረዋል።

ኢዜአ እንደዘገበው ስልጠናው ለተከታታይ አስራ አንድ ቀናት የሚሰጥ ይሆናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *