
ሰሞኑን በተፈጠረው የሲስተም ችግር መነሻነት በሚፈጠር የአገልግሎት ከፍያ መዘግየት ምክንያት ተጠቃሚዎች አገልግሎት እንደማይቋረጥባቸው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።
ካለፉት ሦስት ቀናት ጀምሮ ሲስተም ላይ ባጋጠመ ቴክኒካል ችግር ምክንያት 905 እና 904 ነፃ የጥሪ ማዕከሎች እንዲሁም የዲጂታል ክፍያ አማራጮች ላይ የአገልግሎት መቋረጥ ማጋጠሙን አገልግሎቱ አስታውሷል።
የተቋረጠውን አገልግሎት በአጭር ጊዜ ለመመለስ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን እና ደንበኞች ያጋጠመውን ችግር በመረዳት የተቋረጠው አገልግሎት እስከሚመለስ ድረስ በትዕግሥት እንዲጠብቁም በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ ባሰፈረው መልዕክት ጠይቋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።
