ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከወጪ ንግድ አራት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ዶላር ተመዝግቧል

Spread the love

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የዘጠኝ ወርጨ እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እየገመገመ ይገኛል።

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ እንደገለጹት፤ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የንግድ ከባቢዉን ምቹ ለማድረግ እሰፋፊ ስራዎች ተከናዉነዋል።

በዚህም በኢትዮጵያ በዉጪ ንግድ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ አራት ነጥብ አምስት ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ማስመዝገብ ተችሏል ብለዋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኑሮ ዉድነቱን ለማረጋጋት በሰራዉ ስራም በዘጠኝ ወሩ 374 ተጨማሪ የእሁድ ገበያዎች መፈጠሩንና በአጠቃላይ የእሁን ገበያ ቁጥር አንድ ሺ 476 ማድረስ መቻሉን ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያልተገቡ የንግድ ስርአቶች ለማስቆም በተሰሩ ስራዎች ዉጤት መገኘቱና ለአብነትም የሲሚንቶ ዋጋ በግማሽ እንዲቀንስ ማድረግ መቻሉን ጠቅሰዋል ሲል ኢፕድ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *