የመንግስትና የንግዱ ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት በቅንጅት መስራት ህገወጥና ኮንትሮባንድ ንግድን ለመከላከል ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ

Spread the love

የመንግስትና የንግዱ ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት በቅንጅት መስራት ህገወጥና ኮንትሮባንድ ንግድን ለመከላከል ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ

ህጋዊ የንገድ ስርዓት ተጠናክሮ እንዲቀጥልም በንግድ ዘርፍ ማህበራት የዕለት ተግባር በማድረግ እንደሚሰራም ተጠቁሟል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ነግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ከክልሉ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት ጋር የሁለትዮሽ ውይይት በሚዛን አማን ካሺኒን ሆቴል አድርገዋል።

በዚሁ መድረክ የተሳተፉ የምክርቤቱ አባላት በሰጡት አስተያየት የክልሉ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት ከተቋቋመ ወዲህ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸዋል ።

የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት ምክትል ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ታምራት ታደሰ ለክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን በሰጡት አስተያየት ምክርቤቱ ከተቋቋመ ወዲህ የግንኙነት አግባቡ ከንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ያለፈ እንዳልሆነ ተናግረዋል ።

አሁን ላይ የተፈጠረው የውይይት መድረክ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በቅንጅት መስራት የምንችልበትን ዕድል የፈጠረ ስለመሆኑም አቶ ታምሩ ተናግረዋል ።

ከተቋማት ጋር በቅንጅት መስራት የነጋዴውን ንቃተ ህሊና ከፍ በማድረግና ከሌሎች አቻ ነጋዴዎች ጋር ተፎካካሪ ሆነው ህገወጥ ንግድና ኮንትሮባንድ ንግድን በመቆጣጠር ከኢኮኖሚው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታን ይፈጥርልናል ብለዋል።

ህገወጥነትና ኮንትሮባንድ ንግድ መነሻው ንግድን በዕውቀት አለመምራት ነው ያሉት አቶ ታምሩ ዘመናዊ አሰራሮችን በመከተል ህገወጥነትን ለመከላከል ቅንጅታዊ አሰራር መኖር ወሳኝ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

የንግድና ዘርፍ ምክርቤት የቦርድ አባልና የቴፒ ከተማ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት ጸሐፊ የሆኑት አቶ ዋለ አያሌው በበኩላቸው ተቀራርቦ መስራት ህገወጥነትን ለማምከን ያግዛል ብለዋል።

የተፈጠረው የጋራ ውይይት ህጋዊ ነጋዴዎችን የበለጠ ተጠቃሚ የሚያደርግና ህገወጥነትን የሚያስቀር በመሆኑ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ቢደረግ የተሻለ ይሆናል ሲሉ ገልጸዋል ።

የክልሉ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት ፕሬዚዳንት አቶ አንተነህ አዲሱ በሰጡት አስተያየት በህግ ማህቀፍ የተደራጀ መሆኑን በመግለጽ የንግዱ ማህበረሰብ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚጫወቱት ሚና የላቀ በመሆኑ የመንግስትን አቅም ከፍ የሚያደርጉ መሆኑን ተናግረዋል ።

የንግድና ዘርፍ ማህበራት በተፈጠረው አደረጃጀት በነጻነት የንግድ ግብይቱ የተሳለጠ እንዲሆን የሚያስችል ሲሆን እስካሁን ያሉ ክፍተቶችን በማጥበብ የበለጠ ወደ ውጤት ለመድረስ የሚያግዝ ውይይት መደረጉን አንስተዋል።

የግሉ ዘርፍ በሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ደረጃ ከማምረት እስከ ላኪና አስመጪ የንግድ ልውውጥ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸውም አቶ አንተነህ ገልጸዋል ።

ከመንግስት ጋር ተቀራርቦ መስራት የንግዱ ማህበረሰብ ይበልጥ ተጠቃሚ ይሆናልም ብለዋል አቶ አንተነህ ።

የክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ከበደ በበኩላቸውም የንግድ ዘርፍ ማህበራት ህገወጥ ንግድን ከመከላከል አኳያ ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል ።

ከንግድና ዘርፍ ማህበራት ጋር ተቀራርቦ መስራቱ መብታቸውን ለማስጠበቅና ችግሮችን ተወያይቶ ለመፍታት ያግዛል ብለዋል።

ህጋዊ ነጋዴዎች እንዲበረታቱና ህገወጥ ነጋዴዎች እንዲከስሙ ለማስቻል የንግድና ዘርፍ ማህበራት ድርሻቸው የጎላ መሆኑንም ተናግረዋል ።

የክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ከንግድና ዘርፍ ማህበራት ጋር ተቀናጅተው ለመስራት የሚያስችላቸውን የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል ።

በታጠቅ አበበ

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌በሊንክደን

https://www.linkedin.com/company/southwest-communications

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *