





በደቡብ ሬዲዮና ቴለቪዥን ድርጅት የማሻ ቅርንጫፍ ጣቢያ የ2016 ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በማሻ ከተማ ተካሂዷል።
የደቡብ ሬዲዮና ቴለቪዥን ድርጅት 11ኛ ቅርንጫፍ ሆኖ በቅርቡ የተደራጀው የማሻ ቅርንጫፍ ጣቢያ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከሚገኙት የሚዲያ ተቋማት አንዱ ሲሆን ቅርንጫፍ ጣቢያው የተቋቋመው በቅርቡ ቢሆንም በአድማጩና ተከታዩ ዘንድ የተሻለ ተቀባይነት በማግኘት በክልሉ ካሉት ሚዲያ ተቋማት ጋር ተወዳዳሪ ከመሆን ባለፈ ተመራጭ ለመሆን ብዙ ሥራዎችን በማከናወን ለይ እንደሚገኝ ተጠቁሞዋል።
የተቋሙን የእስካሁኑን አጠቃላይ እንቅስቃሴ በአፈጻጸም ሪፖርት በጣቢያው ዕቅድ ዝግጅት ለውጥ ግምገማ አስተባባሪ በአቶ አስረስ በቀሌ የቀረበ ሲሆን በሰነዱ መነሻ ሰፊ ውይይትና ምክክር ተደርጎዋል።
ተሳታፊዎች በአስተያየታቸው ተቋሙ ከተቋቋመበት አጭር ጊዜ ውስጥ ለዞኑና አጎራባች አካባቢዎች የመረጃ ተደራሽ እየሆነ ያለ ሚዲያ ነው ብለዋል።
የማሻ ኤፍ ኤም 103.8 ስራ ከጀመረ በኃላ ህብረተሰቡ ሚዲያውን በመጠቀም የተለያዩ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በሬዲዮ እያቀረበና ድምፅ በመሆን ምላሽ እያስገኘ ይገኛል ነው ያሉት።
ጀማሪ ሚዲያ በመሆኑ የባለድርሻ አካላት ድጋፍና ክትትል በበቂ ሁኔታ ሊኖር ይገባል ስሉ ጠቁመዋል።
በዞኑ በሚገኙ አንዳንድ አካባቢዎች የተደራሽነት ችግሮች በመኖራቸው መደመጥ የሚችልበት ሁኔታ እንዲመቻች ጠይቀዋል።
በተለይ የተቋሙ ሰራተኞች ለሚዲያው የሚያስፈልግ ቁሳቁስ ባልተሟለበት ለነዋሪዎች መረጃ ተደራሽ እንድሆን እየሰሩ በመሆናቸው ልመሰገኑ ይገባል ስሉ ተናግረዋል።
በደቡብ ሬድዮና ቴለቪዥን ድርጅት ማሻ ቅርንጫፍ ምክትል ስራ አስኪያጅና የይዘት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታደሰ ጋረፎ ተቋሙ በአጭር ጊዜ ባልተሟላ ቁሳቁስ ብዙ ስራዎችን መስራቱን እና የታዩ ክፍተቶችን ወደፊት የሚያስፈልገውን መሳሪያዎችን በሟሟላት እንደሚሰራ ጠቁመዋል።
በደቡብ ሬድዮና ቴለቪዥን ድርጅት ማሻ ቅርንጫፍ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ታምሩ ጉዱ በበኩላቸው ተቋሙን በዞኑ ለማቋቋም ብዙ ፈተናዎች መታለፋቸውን አንስተው ዕውቀትን ባማከለ የሰው ሀይል መደራጀቱን አብራርተዋል።
በሶስት መንገድ ለሕብረተሰቡ መረጃ ተደራሽ እየሆነ እንዳለ በመግለፅ ተቋሙ በበለጠ ለማዘመንና ተወዳዳሪ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት እየተሰራ እንዳለ ጠቁመዋል።
አሁን ላይ ከአካባቢው አልፎ አዲስ አበባ ላይ በጥራት እየተደመጠና በቅርበት በጥራት በማይደመጡ አካባቢዎች ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመፍታት እየተሰራ ነው ብለዋል።
የሸካ ዞን ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ትዕግስት ከበደ በበኩላቸው ለበርካታ ዓመታት የህዝብ ጥያቄ የነበረው የሚዲያ ተደራሽነት ጉዳይ ምላሽ በማግኘት የመረጃ ተደራሽ መሆን ችለዋል በማለት የተደራሽነት ክፍተት ለመሙላት መደገፍ ባለብን መንገድ እንደ ዞን እንደግፋለን ያሉ ስሆን ለሚዲያው የሚያስፈለገውን ቁሳቁስ ለሟሟላትና ለሚዲያ አስፈላጊውን መረጃ ለማቅረብ ትብብር ይደረጋል ማለታቸውን የዘገበው የማሻ ኤፍ ነው።
