




ሰላማዊ መፍትሄና ህግ የማስከበር ስራ እንዴት ተጣጥሞ ይሄዳል፤ለታጣቂዎችና ለፅንፈኛ ሀይሎች ድጋፍ የሚያደርጉ ፓርቲዎችና አካላትን መንግስት የሚታገሰው እስከ መቼ ነው። በኢንቨስትመንት መሬት አቅርቦት ዙሪያ ያሉ ብልሹ አሰራሮችን ለማስተካከል ምን ታስቦዋል እንዲታረሙስ ምን ታስቦዋል፣
ገዢ ትርክት እንዴት መገንባት ይቻላል፣ ብልሹ አሰራሮችን ለማረምና ለማስተካከል ምን ታስቧል፣ መፈናቀል፣ አግባብነት የሌለው የቤት ፈረሳ አሁን በኮሪደር ልማት ምክንያት የተለያዩ ችግሮች አሉን እነዚህን ለማረም ምን እንዴት እየተሰራ ነው፣ ዜጎች በነጻነት ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው እንዲሰሩ የሚደረገው መቼ ነው፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ 8.4 በመቶ እንደሚያድግ ይጠበቃል፣ ይህንን ለማሳካት በብዝሀ ዘርፍ ምን ለማከናወን ታሰቧል የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎች እየቀረቡ ነው።
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ በፌደራልና በክልሎች መካከል ያለው የኢንቨስትመነት አሰራር ላይ ብልሹ አሰራር እንዳለና በቀጣይ እንደሚቀረፍ ተናግረው ነበር፤ ብልሹ አሰራሩን ለመቅረፍ ምን ታሰቧል፣ በሀገራችን ያለውን ችግር ለመፍታት መንግስት እየሔደበት ያለው ወዳታደራዊ መፍትሐየ ነው፣ ሌሎችን መፍትሔዎችን ተግባራዊ ማድረግ ለምን አልተቻለም የሚሉ ጥቄዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀርበዋል።
ከምክር ቤቱ አባላት በቀረቡ ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ።
