የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በቤንች ሸኮ ዞን በሚዛን አማን ከተማ የልማት ስራዎችን ጎበኙ

Spread the love

​ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በቤንች ሸኮ ዞን በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር በፌደራል፣ በክልል፣ በዞንና በከተማ አስተዳደር ደረጃ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን የመስክ ምልከታ አድርገዋል።

​በጉብኝቱ ላይ ሚኒስትሯን ጨምሮ የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን፣ የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሐብታሙ ካፍትን፣ የሚዛን አማን ከተማ ከንቲባ ኢንጅነር ሰለሞን ሌዊ ጨምሮ የክልል፣ የዞንና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

​​የዴንቢ ኢኮ ሎጂ ሀይቅ በቅርቡ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት የሆነው ይህ የቱሪስት መዳረሻ በልዑካን ቡድኑ የተጎበኘ ሲሆን፣ የአካባቢውን የተፈጥሮ ሀብት ለልማት በማዋል ረገድ ያለውን ሚና ተመልክተዋል።

ሌላው በቅርቡ ተገንብቶ ለአገልግሏት የሚጀምረው ​የሚዛን አማን ኢንተርናሽናል ኤርፖርት የትራንስፖርትና የንግድ እንቅስቃሴን ለማቀላጠፍ እየተከናወነ ያለውን የመሰረተ ልማት ዝርጋታ የጉብኝቱ አካል አድርገዋል።

​የሚዛን አማን የኮሪደር ልማት የከተማዋን ገጽታ ለመቀየርና ለነዋሪዎች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የተሰሩ የኮሪደር ልማት ስራዎች ተጎብኝተዋል።

​ልዑካን ቡድኑ በዞኑና በከተማ አስተዳደሩ እየተከናወኑ የሚገኙ ሌሎች የልማት ስራዎችንም የተመለከተ ሲሆን፣ እነዚህ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያላቸውን ፋይዳ ገምግመዋል።

​ሚኒስትሯና ከፍተኛ አመራሮቹ በቆይታቸው በዞኑ በተሰሩ ስራዎች ላይ ያላቸውን ምልከታና በቀጣይ መከናወን ስላለባቸው ተግባራት አቅጣጫ ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል የሚዛን አማን ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *