የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ኢትዮጵያ ፈታኝ ወቅት ላይ በነበረችበት ጊዜ ከጎኗ በመቆም እውነተኛ አጋርነቷን ያስመሰከረች ሀገር ናት – ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)

Spread the love

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ ሼህ ሻክቡት ቢን ናህያን አል ናህያን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ኢትዮጵያ ፈታኝ ወቅት ላይ በነበረችበት ጊዜ ከጎኗ በመቆም እውነተኛ አጋርነቷን ያስመሰከረች ሀገር እንደሆነች ዶ/ር ጌዲዮን ገልጸዋል።

የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት እና የሕዝቦቹን ወንድማማችነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እንደሚሠሩም ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ ሼህ ሻክቡት ቢን ናህያን አል ናህያን በበኩላቸው፥ ዶ/ር ጌዲዮን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው የተሰማቸውም ደስታ በመግለጽ ለሁለትዮሽ ግንኙነቱ ወደ ላቀ ደረጃ መድረስ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ሁለቱ ወገኖች ባደረጉት ውይይት በኢንቨስትመንት እና ንግድ ዘርፍ ያለውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ የሚያስችል አሠራር ለመመስረት ተስማምተዋል።

ሁለቱ ባለስልጣናት ባደረጉት ውይይት በአካባቢያዊ እና ቀጣናዊ የሰላም እና ደኀንነት ጉዳዮች ዙሪያም መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *