ዓድዋ የህብረትና የአንድነት ምልክት መሆኑ ተገለፀ

Spread the love

በኮንታ ዞን 129ኛው የዓድዋ ድል በዓል “ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል” በሚል መሪ ቃል በፓናል ውይይትና በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።

የዕለቱን መልዕክት ያስተላለፉት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አማካሪ አቶ ብርሃኑ ተፈሪ ድሉ ከኢትዮጵያዊያን የወል ታሪኮች መካከል ታላቁ ታሪክና ግዝፈቱም የዓለምን የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ የሰበረ፣ የፀረ-ቅኝ ትግል አቅጣጫን የጠቆመና የታሪክ ቢያኔ የቀየረ ሀቅ ነው ስሉ ተናግረዋል።

አቶ ብርሃኑ የአባቶቻችንን የድል በዓል እያሰብን የተጋረጠውን ድህነት ድል ለመንሳት በሀገሪቱ የተጀመረውን ሁሉአቀፍ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ውጤታማ በማድረግና ለተግዳሮቶች የጋራ መፍትሄ በማበጀት ለዞን፣ ለክልል ብሎም ለሀገር ዕድገት አሻራችንን ሊናሳርፍ ይገባናል ስሉ አስገንዝበዋል።

ለፓናል ውይይት የተዘጋጀውን ሰነድ ያቀረቡት የዞኑ ሰላም፣ ፀጥታና ሚሊሻ መምሪያ ኃላፊ አቶ እስራኤል ጮንቄ ከ15ኛው እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ድረስ ገናና የነበሩ አውሮፓ ሀገራት አሜሪካን ጨምሮ እስያና አፍሪካ ሀገራትን በቅኝ ግዛት አስተዳድረው እንደነበር አስረድተው ሀገራችን ኢትዮጵያ ግን የዓለም የድል ተምሳሌት ሆና ጠላቷን ድል የነሳች ሀገር ስለመሆኗ ገልፀዋል።

ይህ የአድዋ ድል በዓል መላው ኢትዮጵያዊያን ያላቸውን አንድነትና ህብረትን ለዓለም ያሳዩበት ስለመሆኑ ያነሱት ኃላፊው የዓድዋ ድል የጥንካሬያችንና የአሸናፊነታችን መሠረት መሆኑን በመረዳት ትውልዱ ለሀገር አንድነት ግንባታና ብልጽግና የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

የፓናል ውይይቱ ተሳታፊዎች የዓድዋ ድል በዓል ስናከብር ትውልዱ ድህነት ላይ ድል በመንሳት በድጋሚ ማስመስከር ይገባል፤ ይህም የሚሆነው ሁላችንም በየተሰማራንበት የድርሻን ስንወጣ ነው ብለዋል።

ለዚህም በየደረጃው የግንዛቤ ስራዎችን የበለጠ ማሳደግ ይሻልም ነው ያሉት።

በዕለቱ ሌሎች የድል መታሰቢያውን የተመለከቱ መልዕክቶችም ማስተላለፋቸዉን የዘገበዉ የኮንታ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *