በብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባዔ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን ገቢራዊ በማድረግ የክልሉን ህዝብ ዘላቂ የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል።አቶ ማስረሻ በላቸው

Spread the love

የብልጽግና ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው ሁለተኛውን የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ተከትሎ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን ተፈጻሚ ከማድረግና የህዝቡን የልማት ፍላጎት ከግብ ለማድረስ የተያዘውን ቁርጠኝነት አስመልክቶ ከሚዲያዎች ጋር ቆይታ አድርጓል።

በቆይታቸዉ የብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚተገበሩም አብራርተዋል ።

በብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባዔ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን ገቢራዊ በማድረግ የክልሉን ህዝብ ዘላቂ የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራልም ብለዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በአንደኛው የብልጽግና ጉባዔ የተቀመጡ አቅጣጫዎች ሀገርን ያሻገሩና ከመበታተን ወደ አንድነት የሰበሰቡ በርካታ ለውጦች የተገኙባቸው መሆናቸውን አንስተዋል።

በዚህም ሀገራችን ኢትዮጵያ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ትክክለኛ መንገድ ላይ ስለመሆኗም አመላካች መሆኑንም አቶ ማስረሻ ተናግረዋል ።

በአንደኛው የብልጽግና ጉባኤ የተወሰኑ ውሳኔዎች በድል መሳካት መቻላቸው በሁለተኛው ጉባኤ ቀርቦ ስለመገምገሙም አቶ ማስረሻ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል ።

በሁለተኛው የብልጽግና ጉባኤ ስምንት አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል ያሉት አቶ ማስረሻ ከእነዚህም አቅጣጫዎች ሀገራችንን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ተሻለ ከፍታ ለማድረስ የሚያስችል ነው ብለዋል።

እነዚህን አቅጣጫዎች ከግብ ለማድረስም ቁርጠኝነት የታከለበት ከአመራር እስከ ህብረተሰቡ በሕብረ ብሔራዊነት ትርክት ማከናወን ይጠበቃል ብለዋል።

ኢኮኖሚውን ለማስፈንጠር በግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ የጉባኤውን ውሳኔ ተግባራዊ በማድረግ ውጤታማ ስኬቶች ተገኝተዋል ሲሉም በመግለጫው አክለዋል።

በሁለተኛው የብልጽግና ጉባኤ የተቀመጡ አንኳር አቅጣጫዎችን ተከትሎም ፈጠራና ፍጥነት የታከለበት ተግባር በመከወን ኢኮኖሚውን ለማስፈንጠር ብዝሃ _ኢኮኖሚ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባልም ብለዋል።

በዚህም ረገድ በኢንዱስትሪው ፣በግብርና፣በማዕድን ፣በቱሪዝም ፣ በድጂታል ኢኮኖሚውና በሌሎች መስኮች የተጀመሩ ዕድገቶችን የማስቀጠል ስራ ትኩረት ተሰጥቶት ይሰራልም ብለዋል።

በእዚህ ዘርፎች ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራም አቶ ማስረሻ ተናግረዋል ።

የየዘርፉ ምርትና ምርታማነት ሲያድግ የሀገሪቱ የማክሮ ኢኮኖሚ ግብ እንዲሳካ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ግቦችን ለማሳካት የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ እንዲኖር ማድረግ ያስፈልጋል፣ዘላቂ የልማት ፋይናንስ በሀገሪቱ ትኩረት ተደርጎ ቀጣይነት ባለው መልኩ ይተገበራል ሲሉም ተናግረዋል ።

የመጀመሪያው ጉባኤ ውሳኔዎችን ተከትሎ ባሳለፍነው 3 ዓመታት ቀጣይነት ያለው 7.2 ከመቶ ዕድገት መመዝገቡንና በቀጣይም እስከ ጉባኤ ድረስ በአማካይ 8.4 ከመቶ ዕድገት ለማስመዝገብ በትኩረት ይሰራልም ብለዋል።

ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ሪፎርምን የማስቀጠል ስራ ተጠናክሮ ይሰራልም ብለዋል።

እንደሀገር የተጀማመሩ ሜጋ ፕሮጀክቶችን እና በየአካባቢው የተጀመሩየልማት ውጥኖች ውጤታማ እንዲሆኑ ይሰራል ።

ከዚህም ባሻገር የመንግስት ወጪን በመቀነስም ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ሀብት አሟጦ የመጠቀም ስራም ይሰራል ብለዋል።

ኢኮኖሚውን ለማሳደግም ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት የመተካት ስራ በስፋት እንደሚሰራም አቶ ማስረሻ ተናግረዋል ።

ለውጭ ንግድ የሚቀርቡ ምርቶችን በጥራት፣በስፋት የማምረት ስራው ተጠናክሮ እንደሚሰራበትም አቶ ማስረሻ ተናግረዋል ።

ቀጠናዊ ትብብርን በማስፋት ጠንካራ የፊሲካል ፖሊሲን በመተግበር የኑሮ ውድነትንና የዋጋ ግሽበትን ለማርገብ ምርትና ምርታማነትን የማሳደግ፣የሀገር ውስጥና የውጭ ጫናዎችን የመቀነስ፣የበጀት ጉድለት ከ3ከመቶ በላይ እንዳይሆን ትኩረት ተሰጥቶት ይሰራልም ብለዋል በመግለጫቸው ።

ባለፉት ጊዜያት ገቢን የማሳደግ ስራዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው መሰራታቸውን የገለጹት አቶ ማስረሻ በታክስ ገቢ 24 ከመቶ፣ታክስ ባልሆኑ ገቢዎች 28 በመቶ ማደጉንና ምርትና ምርታማነት ተጣጥሞ እንዲያድ የማድረጉ ስራ ትኩረት እንደሚሰጠውም ተናግረዋል ።

ባለፉት 3 ዓመታት ከ9.1 ሚሊዮን በላይ የዜጎች የስራ ዕድል ተጠቃሚነት የተረጋገጠበት መሆኑንና ይህንንም የማስቀጠሉ ስራ እንደሚጠናከር ገልጸዋል ።

እንደ ሀገር በግብርናው ዘርፍ ባለፉት 3 ዓመታት 6.5 በመቶ ዕድገት መመዝገቡንና ከ1.2 ቢሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱንም እንዲሁ ገልጸዋል ።

እንደሀገር በስንዴ ምርት ከአንደኛው ጉባኤ በፊት የነበረው 1.3 ሚሊየን ኩንታል ምርት የነበረው አሁን ላይ ከ 2ኛ ጉባኤው በፊት 107 ሚሊዮን ኩንታል ማድረስ ተችሏል ያሉት አቶ ማስረሻ በቀጣይም 2017 መጨረሻ ላይ 207 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

ከዚህም ረገድ አሲዳማ መሬቶችን በኖራ የማከም፣የመካናይዜሽን እርሻን የማጠናከር ፣የግብርና ስራዎችን ባህል የማድረግ ተግባር ትኩረት ይሰጠዋል ብለዋል።

ኢንዱስትሪውን ዘርፍ ከማነቃቃት አንጻር በምግብ ራስን ከመቻል አልፎ ለኢንዱስትሪ ደጋፊ ምርት ማምረት፣ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ስራዎች ፣ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ የኢንዱስትሪ መሠረተ ልማት ዝርጋታ፣በቂ የፋይናንስ አቅርቦት ማመቻቸት፣የእርስ በርስ ትስስርን የማጠናከር ስራዎች ትኩረት ይሰጣቸዋል ብለዋል።

በኢኮኖሚው ዘርፍ መዋቅራዊ ለውጥ በሚያመጡ እንደ ቱሪዝምና የቱሪዝም አገልግሎት አሰጣጡን የማዘመን፣ድጂታል ኢኮኖሚውን የማሳደግ የመሠሰተ ልማት አውታሮችን በጥራት፣በቅልጥፍናና በፍትሐዊነት የማከናወን ተግባር ይጠናከራል ሲሉም ገልጸዋል።

የከተማና የገጠር ኮሪደር ስራዎች ለብልጽግና ምሳሌ በሚሆን መልኩ ተጠናክረው ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል።

እንደክልል ከሀገራዊ ኢኒሼቮች በተጨማሪ በክልሉ አዳዲስ ኢኒሼቲቮች ተግባራዊ እንደሚደረጉም አቶ ማስረሻ ተናግረዋል ።

የሌማት ትሩፋት፣የበጋ መስኖ ልማት ስራዎች የኮሪደር ልማት ስራዎችን ተከትሎም በቡና ልማት፣በሻይ ልማት፣ በሩዝ ምርት፣በማር ምርታማነት፣በፍራፍሬ ልማት በተለይም በአቮካዶ ምርታማነት፣በቅመማ ቅመም በተለይም ኮረሪማ ምርታማነት ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ አክለዋል ።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *