የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ፈጠራ፣ ፍጥነትና ዝላይ እሳቤዎችን በመላበስ በቁርጠኝነት መተግበር ይጠይቃል

Spread the love

የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ፈጠራ፣ ፍጥነትና ዝላይ እሳቤዎችን በመላበስ በቁርጠኝነት መተግበር ይጠይቃል ሲሉ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰብለ ጸጋ አየለ ገለጹ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት የ200 ብር ለእናቴ ንቅናቄ የሃብት አሰባሰብ ዙሪያ ማስጀመሪያ መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በንቅናቄው መድረክ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት ወ/ሮ ሰብለጸጋ አየለ የብልጽግና ፓርቲ በሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ያስቀመጠውን አቅጣጫና ውሳኔዎችን በማጽናት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ገለጸዋል።

የሴቶች ከንፍ የመደመር ዕሳቤን መሰረት በማድረግ ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የወሰደዉን ተልዕኮ ከማሳካት አኳያ ስኬታማ ጉዞ እያደረገ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።

የሴቶች ተሳትፎ፣ ተጠቃሚነትና አበርክቶ በህዳሴ ግድብ ፣በአረንጓዴ አሻራ ፣በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ፣በጤናና በበጎ አድራጎት በሌሎች ዘርፎች ላይ አይተኬ ሚና ተጫውተዋል።

እስካሁን በሴቶች ክንፍ አስተባባሪነት የተገኙ ስኬቶች እንደመስፈንጠሪያ አቅም በመጠቀም ሴቶች ካለባቸዉ ሰፋፊ ነባራዊ ችግሮች አኳያ በመነሳት በፓርቲያን የተፈጠሩትን ምቹ ዕድሎች በመጠቀም ፈጠራ፣ ፍጥነትና ዝላይ እሳቤዎችን ተላብስሶ በቁርጠኝነት መትጋት ይጠበቃል ብለዋል።

በዚህም ገቢ ማስገኛ የሌላቸው እናቶችን በቋሚነት ገቢ የሚያገኙበትን የስራ ዕድል በመፍጠር ኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥና ከተረጂነት ለማለቃቅ ከምንም ጊዜ በላይ በትጋት መስራት ይጠበቃል። ብለዋል።

በክልሉ ያለውን ሀብትና ፀጋዎችን አማጦ በመጠቀም በከተማና በገጠር ለሚገኙ እናቶችን ስራ ዕድል መፈጠር ይጠበቃል ያሉት ወ/ሮ ሰብለጸጋ ማህበራዊና ኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ብርቱ ትግል ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል።

የሀብት አሰባሰብ ስራውን ሁለም በየደረጃው ያሉ የሴቶች አደረጃጀቶች በቁርጠኝነት እንዲሰሩ አሳስበዋል የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *