ዓተ ምግብ ሽግግር ፍኖተ ካርታዉ በሥርዓተ ምግብ ምክንያት የሚፈጠሩ የመቀንጨር እና ሌሎች ተያያዥ ችግሮችን የሚፈታ መሆኑ ተመላከተ

Spread the love

ይህ በክልሉ ለቀጣይ አምስት ዓመታት የሚተገበረው ሥርዓተ ምግብ ሽግግር ፍኖተ ካርታ ይፋዊ ማስጀመሪያ መርሐግብር የክልሉ ርዕሰ መስተዳር ልዩ አማካሪ አቶ ሰብስቤ ሸዋኖ እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል።

በክልሉ የምግብ ሉዓላዊነትን እንዲረጋገጥ የግብርና ምርታማነት መጨመር የሚያስችሉ ግብዓቶችን በተሟላ መልኩ መጠቀም እንደሚገባም ያስረዱት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ልዩ አማካሪ አቶ ሰብስቤ ሸዋኖ በዚህም የአመጋገብ ሥርዓትን በማስተካከል ጤናማና ብቁ ዜጋ እንዲፈጠር ትኩረት ይደረጋልም ብለዋል።

የተዘጋጀው ፍኖተ ካርታ ውጤታማ የሚኾነው ተቋማት ተቀናጅተው ሲሰሩና ተግባሩን የዕቅዳቸው አካል በማድረግ በበጀት ማስደገፍ ሲችሉ እንደኾነም ጠቁመው ዘርፉ በርካታ ተዋናዮች የሚሳተፉበት በመኾኑ ሁሉም አካላት ተቀናጅተው መሥራት እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል።

ሥርዓተ ምግብ ሽግግር ፍኖተ ካርታዉ በሥርዓተ ምግብ ምክንያት የሚፈጠሩ የመቀንጨር እና ሌሎች ተያያዥ ችግሮችን የሚፈታ መሆኑንም የርዕሰ መስተዳድሩ ልዩ አማካሪው አመላክቷል።

በክልሉ በምግብ ሥርዓት እና ሥርዐት ምግብ እጥረት ምክንያት የሚከሰቱ የጤና ቀዉስ በመከላከል ጤናማና አምራች ዜጋ እንዲፈጠር በሚደረገው እንቅስቃሴ የክልሉ ጤና ቢሮ ሚናውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለጹት የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሙልቀን አሰፋ ናቸዉ።

በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ግብርና ቢሮ ተወካይ አቶ ግርማ ጆቴ በበኩላቸው በክልሉ የተጀመሩ የተለያዩ የግብርና ኢንሼቲቭ አጀንዳዎችን በመፈጸም የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ሥርዓት ሽግግር ፍኖተ ካርታ ውጤታማ እንዲሆን በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

የፍኖተ ካርታ ማስጀመሪያ መረሐ ግብር ተሳታፊዎች በበኩላቸው ተግባሩ ከምግብ ምርት ጀምሮ እስከ አቅርቦትና አጠቃቀም ድረስ ያለውን ሂደት በማስተካከል የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ ጤናማና ተመጣጣኝ ምግብ ለህዝባችን እንዲደርስ የሚያግዝ በመሆኑ ለተግባራዊነቱ የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ ገልጸዋል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *