












የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።
በምረቃ ስነ-ስነ ስርዓቱ ላይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦቸ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፀጋዬ ማሞ ተመራቂ ተማሪዎችን እንኳን ደስ አላችሁ ብለው ምሩቃን የተሻለ ባገኙት እውቀት ለሀገር እድገትና ብልፅግና የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ዩኒቨርሲቲው በሁሉም መስክ በመሻሻል ላይ ነው ያለው ያሉት አቶ ፀጋዬ ማሞ አዲሱ በዩኒቨርሲቲው የተደራጀው ማናጅመንት በቆራጠኝነት ማገልገል ላይ በመሆናቸው አመስግነዋል።
ሀገራችን የህዝቦቿን ብልጽግናን ለማረጋገጥ ሰፊ ስራዎችን በማከናወን ላይ መሆኗን ጠቁመው ምሩቃን በዚህ ጉልህ ሚና ስላላቸው ለሀገራቸው ተጨማሪ አቅም መሆን እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
ዶክተር ዋቆ ገዳ እንደተገለጹት ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ሥራው ባለፈ ችግር ፈቺ የምርምር ተግባራትን ለማከናወን እየሰራ መሆኑንም አስረድተዋል።
ዛሬ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ ድግሪ የሚመረቁ መሆናቸውን ገልፀው ከተመራቂ ተማሪዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተናን በጥሩ ውጤት ያለፉ ናቸው ብለዋል።
በዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች የተመረቁት 1 ሺህ 279 ተማሪዎችን መሆናቸው ልፀው ከተመራቂዎች መካከል 1 መቶ 79 በሁለተኛ ዲግሪ መሆኑ ገልፀዋል።
ተመራቂዎቹ በግብርና፣ በጤና ፣ በሕግ እንዲሁም በተለያዩ የትምህርት መስኮች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ናቸው ብለዋል።
የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትንን በበኩላቸው ተመራቂ ተማሪዎች በትምህርት ዘመናችሁ ያጋጠሟችሁን መሠናክሎች ተሻግራችሁ ለዛሬው የደስታ ቀን በመብቃታቾሁ እንኳን ደስ አላችሁ” ብለዋል።
መንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን በተለያዩ የትኩረት መስኮች እንዲያተኩሩ በማድረግ ከፍተኛ ስራ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የለውጥ ሃሳቦችን በማፍለቅና በመተግበር መልካም አርአያ የሚሆኑ ዜጎችን ማፍሪያ፣ የዲሞክራሲያዊ አስተሳሰቦችና ቴክኖሎጂዎች መፍለቂያ፣ የባህላዊ እሴቶቻችን መጎልበቻ፣ የሕዝቦች የመተሳሰብ፣ የመቻቻልና የአብሮነት ባህል የሚቀመርባቸው ማዕከላት ናቸው ብለዋል።
ምሩቃን ሥራ ወዳድና ታታሪ፣ በሕግ የበላይነት ላይ የማትደራደሩ፣ በሥነ-ምግባር የታነጻችሁ ሀገር ተረካቢ ብቻ ሳትሆኑ አሻጋሪም ጭር ናችሁ ብለዋል።
በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ አምባሳደር አል ቡሲራ ባስኑር በኢትዮጵያ ጅቡቲና የአፍሪካ ህብረት የኢንዶኔዥያ ሪፐብሊክ አምባሳደር ፣ የተመራቂ ቤተሰቦች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል።
