የብሔር ብሔረሰቦች ቀን መከበር ህብረ-ብሄራዊ አንድነትን በማጎልበት የጋራ ትርክትን ለመገንባት ፋይዳው የጎላ መሆኑ ተገለፀ

Spread the love

‎20ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል “ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረብሄራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል በቦንጋ ከተማ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች በድምቀት ተከብሯል፡፡

‎በዓሉ በኢትዮጵያ ህዝብ ብሔረዊ መዝሙር የተጀመረ ሲሆን ለበዓሉ የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ ውይይት የተደረገ እና የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር ተካሂዷል፡፡

‎በዓሉ በየዓመቱ መከበሩ የህዝቦችን ትስስር ከማጠናከሩም በላይ ህብረ-ብሄራዊ አንድነትን በማጎልበት የጋራ ትርክትን ለመገንባት ፋይዳው የጎላ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

በበዓሉ አከባበር ላይ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ንጉሴ ወ/ጎርጊስ፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ባህሎችና እሴቶች መገኛ መሆኗ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ሲናከብር ትውልድ ተሻጋሪ የሆነ ህብረ ብሔራዊ አንድነት ለመፍጠር የብሔር ብሔረሰቦች የጋራ ርብርብ ያስይፈልጋዋል ብለዋል።

በፖለቲካ ስርዓት ግንባታው ላይ በተለይም ዴሞክራሲን ከማስፈን አኳያ መንግሥት ሚናውን እየተወጣ መሆኑንና በዚህም የህብረተሰቡ ተሳትፎ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ገልፀዋል፡፡

የካፋ ዞን ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ አቶ እሼቱ ወጋሳ በበኩላቸው የዘንድሮው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን የአይችሉም ትርክት ሰብረን ታላቁ የህዳሴ ግድባችንን በደማችንና በላባችን ገድበን ያጠናቀቅንበት በመሆኑ ከወትሮው ልዩ የሚያደርገዋል ብለዋል፡፡

በዓሉ ህብረ ብሔራዊነትን በጋራ በማስተሳሰር ህብረብሔራዊ አንድነትን የሚናበረክተው እሴት መሆኑንና የጋራ እሴት የሆነውን የጋራ ትብብር ለኢትዮጵያ ልማት ማጠናከር እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ለሀገር ግንባታ ያላቸውን ሚና በአግባቡ አውቀው ከዚህ ቀደም የነበሩ የተሳሳቱ ትርክቶችን ማረም የሁሉም ዜጋ ሊሆን እንደሚገባም አንስተዋል፡፡

የዘንድሮ ‎20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ ሕዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አስተናጋጅነት በሆሳዕና ከተማ ይከበራል።

በተከተል ወ/ሚካኤል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *