


የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ባወጣው መግለጫ፣ የ1447ኛው የዒድ አል-ፊጥር በዓል የሸዋል ጨረቃ ዛሬ ምሽት ከታየች ነገ ሐሙስ መጋቢት 10 ቀን 2018 ዓ.ም የሚከበር መሆኑን አስታውቋል።
ሆኖም ዛሬ ምሽት ጨረቃ ካልታየች የረመዷን ፆም 30 ቀናት ተሟልቶ በዓሉ የፊታችን ዓርብ መጋቢት 11 ቀን 2018 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት እንደሚከበር ጠቁሟል።
ፍርድ ቤቱ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቱን ያስተላለፈ ሲሆን፣ በቅዱሱ የረመዷን ወር የታየው የመረዳዳትና የደግነት መንፈስ በበዓሉ ዕለትና ከዚያም በኋላ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የአንድነት እንዲሆንም መልካም ምኞቱን ገልጿል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።
