









ውይይቱ በክልሉ ያለውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በተለይም የጤና፣ የግብርና፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና የሌሎችም ስራዎችን ውጤታማነት ለማረጋገጥ የሚያስችል መግባባት መፍጠርን ዓላማው ያደረገ ነው።
በውይይት መድረኩ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO)፣ የተባበሩት መንግስታት የህፃናት መርጃ ድርጅት (UNICEF)፣ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (OCHA)፣ የተባበሩት መንግስታት የምግብ እና እርሻ ድርጅት (FAO) እና ሌሎችም የተ.መ.ድ. ተወካዮችና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በውይይቱ እየተሳተፉ ነዉ።
