




በስብሰባው ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት የተውጣጣ የልዑክ ቡድን እየተሳተፈ ይገኛል።
በወጣቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ዙሪያ የፓናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ ላይ ኢትዮጵያን በመወከል መልዕክት ተላልፏል።
የልዑካን ቡድኑ ኢትዮጵያ በብሪክስ ማዕቀፍ ውስጥ የመተባበር እና የአንድነት መንፈስ እንዲጎለብት ሚናዋን በተገቢው መልኩ እንደምትወጣ ገልጿል።
ልዑኩ ከስብሰባው ጎን ለጎን የካዛን ከተማ የወጣት ማዕከላት እና የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎችን መጎብኘቱን ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
