በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የምክክር መድረክ ባለድርሻ አካላት አጀንዳዎቻቸውን እያደራጁ ነው፡፡

Spread the love

በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስተባባሪነት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የምክክር መድረክ ባለድርሻ አካላት አጀንዳዎቻቸውን እያደራጁ ነው፡፡

የክልሉ ባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ትላንት ሐሙስ ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም በቦንጋ ከተማ በካፋ ባህል አደራሽ መጀመሩ ይታወሳል፡፡

በዚህ የምክክር መድረክ ከ1ሺ 100 በላይ የሚሆኑ ባለድርሻ አካላት ሲሆኑ ወኪሎቹ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከመንግስት አካላት፣ ከወረዳ ማህብረሰብ ተወካዮች፣ ከተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እና የሀይማኖት ተቋማትን ጨምሮ ከተለያዩ ማህበራትና ተቋማት ተሳታፊዎች የተመረጡ ናቸው።

ከትላንት ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም ጀምረው በቡድን ሲመካከሩ የነበሩ አምስቱ ባለድርሻ አካላት ከእያንዳንዳቸው አምስት ተወካዮችን በመምረጥ በድምሩ 25 ወኪሎችን የክልሉን አጀንዳ እንዲያደራጁ መርጠዋል።

እነዚህ የተመረጡ 25 ወኪሎች የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አጀንዳዎችን አደራጅተውና አጠናቅረው ነገ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም በዋና መድረክ ካቀረቡ በኋላ አጀንዳዎቹን ለኮሚሽኑ የሚያስረክቡ ይሆናል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የምክክር መድረክ ካለፈው እሁድ ጥቅምት 24/2017 ዓ.ም ጀምሮ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል።

በተከተል ወ/ሚካኤል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *