የክልሉ ትምህርት ቢሮ አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በክልሉ በተሳካ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲሆን ሰፊ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ

በክልሉ የኮንታ ዞን በማህበረሰብና በመንግስት ተሳትፎ ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ በማሰባሰብ በኮንትኛ ቋንቋ ያሳተመውን ከ64 ሺ በላይ ከቅድመ 1ኛ እስከ ስድስተኛ ክፍል የመማሪያና የማስተማሪያ መፅሀፍት ርክክብ ተደርጓል። በመድረኩ የተገኙ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ትምህርት ቢሮ አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በክልሉ በተሳካ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲሆን ሰፊ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ የቢሮው ምክትል ሀላፊና ስርዓተ ትምህርት ዘርፍ…

Read More

“ዲፕሎማሲያችን ለብሔራዊ ጥቅማችን” ዓውደ-ርዕይ ነገ በይፋ ይከፈታል

“ዲፕሎማሲያችን ለብሔራዊ ጥቅማችን” በሚል የሚካሄደው የዲፕሎማሲ ሣምንት ዓውደ-ርዕይ በነገው ዕለት በይፋ እንደሚከፈት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም (ዶ/ር) ዓውደ ርዕዩን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም እንዲከበር የሁሉም ሕብረተሰብ ተሳትፎ ሊጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል። አምባሳደር መለስ (ዶ/ር)÷ “ዲፕሎማሲያችን ከአፍሪካ መዲናነት እስከ ዓለም ዓቀፍ መድረክነት” በሚል ሥያሜ በሚካሄደው ዓውደ-ርዕይ ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆኑ…

Read More

የኢትዮ-ሶማሊላንድ የባህር በር ስምምነት በቅንነት የሚወሰድና የሚደገፍ ሀገራዊ አጀንዳ ነው

ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ያደረገችው የባህር በር ስምምነት በቅንነት የሚወሰድ ሀገራዊ አጀንዳ በመሆኑ ለተግባራዊነቱ ድጋፍ እንደሚያደርጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት ተናገሩ። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከአባላቱ ጋር ምክክር አድርጓል። በኢትዮጵያና ሶማሊላንድ መካከል በተደረሰው የመግባቢያ ስምምነት ዙሪያም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ማብራሪያ ሰጥተዋል። ከውይይቱ በኋላ ለኢዜአ…

Read More

ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ

የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በኢትዮጵያና በሶማሊ ላንድ መካከል የተደረሰዉን ስምምነት አስመልክቶ በምክር ቤቱ ሰብሳቢዉ በኩል መግለጫ ሰጥቷል። መግለጫዉን የሰጡት የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን አየለ በኢትዮጵያ እና በሶማሌ ላንድ መካከል የተደረሰዉ ስምምነት ሁሉን አቀፍ የትብብርና አጋርነት የሚያጠናክር በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ፖለቲካዊና ወታደራዊ መስኮች እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆነ ስምምነት እንደሆነ…

Read More