በአገሪቱ የሚገኘውን የገጠር መሬት ምዝገባና ቅየሳ ሥራ አንድ ወጥ ሆኖ በክልሎች እንዲፈጸም የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ እንዲኖር በትኩረት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በረቂቅ አዋጅ ዙሪያ በታርጫ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል። የኢፌዲሪ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 456/1997 ታውጆ ሥራ ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ 19 ዓመታትን አስቆጠሯል። በመሆኑም አገሪቱ ከደረሰችበት የዕድገት ደረጃ እንዲሁም የአርሶና አርብቶ አደሩ ገቢ እያደገ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በመሬት ላይ ያላቸው የመጠቀም መብትን ማሻሻያ እንዲደረግ አስገዳጅ ሁኔታ ተፈጥሯል ተብሏል። የገጠር…
