የክልሉ ምክር ቤት ጉባዔ ከጥር 30/2016 ጀምሮ ሊካሄድ ነዉ::
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ምክርቤት 6ኛ ዙር 3ኛ የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባዔ ከፊታችን ጥር 30/2016 እስከ የካቲት 1/2016 ዓ/ም በታርጫ ከተማ እንደሚካሄድ አስታወቀ። ጉባኤውን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የክልሉ ምክርቤት ዋና አፈ ጉባዔ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ ለጉባኤው አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል ። በዚህም ለጉባኤው ተሳታፊዎች ጥሪ መተላለፉን አፈጉባዔ ወንድሙ ኩርታ…
