የቡና ማሳ አያያዝና ቁጥጥርን በማጠናከር የተሻለ ምርት ለማግኘት እየተስራ መሆኑ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
ባለስጣን መስሪያ ቤቱ በቡና ምርት ማሻሻያ ፓኬጅ ላይ ያተኮረ የአሰልጣኞች ስልጠና በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ እየሰጠ ይገኛል። የቡና ምርት በማሻሻል የቡና አምራች አርሶአደሮችን ከዘርፉ ተጠቃሚ ለማድረግ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እያደረገ ያለው ተግባር የሚደነቅ መሆኑን የገለጹት በመድረኩ በክብር እንግድነት የተገኙት የሸካ ዞን የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ዓለሙ እንደገለፁት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በክልሉ ለቡናና ቅመማ ቅመም…
