“ኢትዮጵያ ውስጥ መንግስታዊ ሙስና የለም”፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Spread the love

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ውስጥ መንግስታዊ ሙስና የለም ነገር ግን ከአገልግሎት አንጻር የሙስና ተግባር አለ።

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በሶስት ወራት ብቻ 23 ተቋማትን በማካተት 124 አገልግሎቶችን እየሰጠ መሆኑን ጠቅሰው፤ የሙስናንና ብልሹ አሰራርን ለመቅረፍ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አሁን አንድ ማዕከል ብቻ ነው ያለው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣እስከ መስከረም ድረስ 17 እናደርሳለን ብለዋል።

መሶብ እየተስፋፋ አገልግሎት እየዘመነ ሲሄድ የእጅ በእጅ ሙስና እየቀነሰ እንደሚሄድም ገልጸዋል፡፡

ሙስናን መፀየፍ የግለሰቦችን አመለካከትና ውሳኔን የሚጠይቅ መሆኑን በመግለጽ፤ ሙስናን የምንከላከለው በስርዓት ነው ብለዋል፡፡

በተዘረጋው የመሶብ ስርዓትም ተገልጋዮች ከ90 በመቶ በላይ እርካታ መሆኑን ጠቅሰው፤ በሁሉም አካባቢዎች ማስፋት ከተቻለ ሙስና በእጅጉ እንደሚቀንስ ገልጸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *