Trendings

በክልሉ የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች ተጠናቅቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ።

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) የታርጫ ማዕከል የክልል ተቋማት ህንፃ እንዲሁም የዳውሮ ባህል ማዕከል አዳራሽ የግንባታ ሂደትን ጎብኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በጉብኝታቸው የክልሉ መንግስት በክልሉ የተለያዩ አከባቢዎች የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች ተጠናቅቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የክልሉ የታርጫ ማዕከል ተቋማት ህንፃ ግንባታ ያለበትን ደረጃ የተመላከቱ ርዕሰ መስተዳድሩ ህንፃው ሲጠናቀቅ የአገለግሎት አሰጣጥን ወደ ተሻለ ደረጃ በማሳደግ የህብረተሰብ ተጠቃሚነትን እንደሚያረጋግጥ አንስተዋል የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል።

በዞኑ ህብረተሰብ ተሳትፎና በመንግስት እየተገነባ ያለው የዳውሮ ብሔር የታሪክ፣ የቅርስና የባህል ምርምር ማዕከል አካል የሆነው የባህል አዳራሽ ግንባታ ሂደት በተሻለ ደረጃ እንደሚገኝ አንስተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *