Trendings

West-Omo Zone

የምዕራብ ኦሞ ዞን ገፅታ በከፊል!!!

የምዕራብ ኦሞ ዞን አጠቃላይ ገፅታ – West Omo Zone Profile

የምዕራብ ኦሞ ዞን አጠቃላይ ገፅታ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት

440,356

አጠቃላይ የሕዝብ ብዛት

14,764 ስኩዌር ኪ.ሜ

የቆዳ ስፋት

7 ወረዳ / 4 ማዘጋጃ

የአስተዳደር መዋቅር

114

የገጠር ቀበሌያት

መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥና ወሰን (Geography & Borders)

የምዕራብ ኦሞ ዞን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በአዲስ ከተደራጁት ዞኖች አንዱ ነው። ዞኑ ስትራቴጂካዊና ሰፊ መልክዓ ምድር ያለው ሲሆን የወሰን አወሳሰኑ እንደሚከተለው የተዋቀረ ነው፡

  • በደቡብ አቅጣጫ፡ ከደቡብ ኦሞ ዞን ጋር ይዋሰናል
  • በደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ፡ ከደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ጋር ዓለም አቀፍ ወሰን ይጋራል
  • በሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ፡ ከቤንች ሸኮ ዞን ጋር ይዋሰናል
  • በሰሜንና በምስራቅ አቅጣጫ፡ ከከፋ ዞን ጋር ይዋሰናል

የህዝብ ብዛትና ስነ-ህዝብ ስብጥር (Demographics & Settlement)

በክልሉ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ትንበያ መረጃ መሰረት፣ የዞኑ ነባር አራት ብሔረሰቦች (የመኤን፣ የዲዚ፣ የሱርማና የዝልማሞ) ጠቅላላ የህዝብ ብዛት 345,209 ነው። ከዚህ ውስጥ 91.1% በገጠር የሚኖር ሲሆን፣ ቀሪው 8.9% በከተማ ይኖራል።

ነገር ግን፣ ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ በጎልዲያና በሻሻ አካባቢዎች በፈቃደኝነትና በክልሉ የሰፈራ ፕሮግራም የመጡ 95,147 ነዋሪዎችን ጨምሮ፣ በአሁኑ ወቅት የዞኑ አጠቃላይ የህዝብ ስብጥር 440,356 ይደርሳል። *(ይህ አሃዝ በቤሮ በረሃ ያሉትንና በማጂና ሱሪ ከተሞች የሚኖሩትን ህዝቦች ሳያካትት ነው)*።

የነባር ብሔረሰቦች የህዝብ ድርሻ ስብጥር፦

ብሔረሰብ (Ethnic Group) የህዝብ ብዛት (Population) የመቶኛ ድርሻ (Percentage)
መኤን (Me’en) 240,564 71%
ዲዚ (Dizi) 66,027 19%
ሱርማ (Surma) 34,808 10% (በጋራ)
ዘልማሞ (Zelmamo) 3,810

አግሮ-ኢኮሎጂና አየር ንብረት (Agro-Ecology & Climate)

የዞኑ መልክዓ ምድር ከባህር ጠለል በላይ ከ 500 ሜትር እስከ 2500 ሜትር ከፍታ የሚሸፍን ሲሆን ተራራማ፣ ረባዳማና ሸለቆማ ቦታዎችን የያዘ ነው። አካባቢው በሶስት ዋና ዋና የአግሮ-ኢኮሎጂ ዞኖች የተከፋፈለ በመሆኑ ለግብርና ስራና ለተለያዩ ሰብሎች ምርት እጅግ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡

  • ቆላማ ቀጠና (Lowland): 52% ይሸፍናል
  • ወይና ደጋ ቀጠና (Midland): 34% ይሸፍናል
  • ደጋማ ቀጠና (Highland): 5% ይሸፍናል

ዞኑ በጋ፣ በልግና ክረምት የሚፈራረቁባቸው ሶስት የዝናብ ወቅቶች አሉት። ዓመታዊ አማካኝ የዝናብ መጠኑ ከ 400 እስከ 2200 ሚ.ሊ የሚደርስ ሲሆን፣ ዓመታዊ አማካኝ የሙቀት መጠኑ ከ 15.1°C እስከ 27°C ይደርሳል።

የማህበራዊና አስተዳደራዊ ልማት እንቅስቃሴዎች (Development & Services)

ያልተማከለ አሰራር፦ የዞኑ መንግስት ለህብረተሰቡ ግልጽ፣ ቀልጣፋና አሳታፊ አገልግሎት ለመስጠት በጀት፣ ስልጣንና የሰው ኃይልን ወደ ታችኛው እርከን በማውረድ በተግባር እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

ገጠርና ከተማ ልማት፦ በአርብቶ አደርና ከፊል አርሶ አደር አካባቢዎች ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በተሰሩ ስራዎች የህብረተሰቡ ኑሮ ተሻሽሏል። በከተሞችም የቤቶች ልማትና በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ዘርፍ ሰፊ ስራዎች ተከናውነዋል።

ትምህርትና ጤና፦ የትምህርት ተደራሽነትና ፍትሃዊነትን በማረጋገጥ ረገድ አበረታች ውጤቶች የተመዘገቡ ሲሆን የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጆች ተቀርፀው በመተግበር ላይ ናቸው። በጤናው ዘርፍም በመከላከል ላይ የተመሰረተ የጤና ፖሊሲን በመከተል የጤና ተቋማትን የማስፋፋት ስራ በስፋት እየተከናወነ ይገኛል።

Nationalities in West-Omo Zone,Me’en, Suri, Diz & Zilmamo

Me’en Nationality

Suri Nationality

Diz Nationality

Zilmamo Nationality