


የችግኝ ተከላውን በሸካ ዞን የኪ ወረዳ አዲስ ብርሃን ቀበሌ በእንድሪስ ሙሉ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተከናውኗል ።
በችግኝ ተከላው የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ፣የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት አፈጉባኤዎች ፣የክልሉ ምክርቤት አፈጉባኤዎች እና የክልሉ ብሔረሰቦች ምክርቤት አባላትና የጉባኤው ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።
በችግኝ ተከላው ኢኮኖሚያዊ ጠቃሜታ ያላቸውን ችግኞች በመትከል ህብረተሰቡ ተጠቃሚ የሚሆንበት ሁኔታ እንዲፈጠር ትኩረት በመስጠት ተከናውኗል ።
