ወደብን በሚመለከት!

Spread the love

የወደብ ጉዳይን አዲስ ጥያቄ አድርገው የሚያነሱ አሉ፤ የጎረቤት አገራትን ሉዓላዊነት ለመጉዳት የተነሳም አስመስለው የሚያቀርቡ አሉ፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ የማንንም አገር ሉዓላዊነት የመጉዳትና የመውረር ፍላጎት የለንም፡፡ ኢትዮጵያ ያልተገባ ጥያቄ ከህግ ውጪ አልጠየቀችም፡፡ ኢትዮጵያ ወደ ጎረቤት አገራት አንድ ጥይት የመተኮስ ፍላጎትም የላትም፡፡ ነገር ግን በህግና በቢዝነስ ማእቀፍ እንወያይ ነው ያልነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ እያደገ ነው፤ በመሆኑም ጉዳዩ ጊዜ ሳይሰጠው አሁኑኑ መፍትሄ ሊበጅለት ይገባል ብለን እናምናለን፤ ረሃብ፣ ችግር ሳይመጣ ተነጋግረን ህጋዊ መፍትሄ እናብጅ ነው ያልነው፡፡ ጥያቄዎን ማንሳታችን እንደ ነውር ሊቆጠርም አይገባም፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *