በጋምቤላ ክልል በሚቀጥሉት አስር ቀናት ከመደበኛ በላይ የዝናብ ስርጭት ይኖራል

Spread the love

በጋምቤላ ክልል በሚቀጥሉት አስር ቀናት መደበኛና ከመደበኛ በላይ የዝናብ ስርጭት ሊኖር እንደሚችል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

ከሚጥለው ዝናብ ጋር ተያይዞ የጎርፍ መፋሰሻዎችን በማጽዳት ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት መከላከል እንደሚገባም ተገልጿል።

በኢንስቲትዩቱ የጋምቤላ ክልል ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ተስፋሁን ዓለሙ ለኢዜአ እንደገለጹት በክልሉ ከሚያዝያ ወር መግቢያ 2017 ጀምሮ ጠንከር ያለ የዝናብ ስርጭት ይኖራል።

በተለይም በክልሉ የወይና ደጋ የአየር ጸባይ ባለው የማጃንግ ዞን የዝናብ ስርጭት መጠኑ ጠንከር ያለ እንደሚሆንም አስታውቀዋል።

በክልሉ የሚኖረው የተጠናከረ የዝናበ ስርጭት ለመኸር እርሻ ማሳ ዝግጅትና ለግጦሽ አወንታዊ ሚና እንደሚኖረውም ገልጸዋል።

በአንፃሩ በክልሉ በሚኖረው የተጠናከረ የዝናብ ስርጭት ምክንያት በከተሞች ጎርፍ ሊያስከትል ስለሚችል የውሃ ማፋሰሻ ቦዮችን ማጽዳትና መክፈት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

እንዲሁም የሚጥለው ዝናብ ወባን ሊያስከትል ስለሚችል ውሃ የሚያቁሩ ቦታዎችን ከወዲሁ ማዳፈን እንደሚገባ አቶ ተስፋሁን ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *