ግብር ከፋዮች ባርኮድ (QR-Code) ያለበትን ደረሠኝ በማሳተም ወደ ተግባር መግባት እንዳለባቸወ ተገለጸ

Spread the love

ከየካቲት 02/2017 ዓም ጀምሮ ነባሩ የእጅ በእጅ ደረሠኝ ጥቅም ላይ ማዋል አስተዳደራዊና ህጋዊ ተጠያቂነት የሚያስከትል እንደሆነ ግብር ከፋዩ ተገንዝቦ አዲሱን ባርኮድ ደረሠኝ እንዲያሳትም ተጠቁሟል።

አቶ ወንዱ ታደሰ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ የቢሮው ምክትል ኃላፊና የደንበኞች አገልግሎት የግብር አወሳሰንና አሰባሰብ ዘርፍ ኃላፊ እንዳሉት ግብር ከፉዩ አሁን ላይ አገልግሎት እየሠጠ ያለውን የማንዋል ደረሠኝ ከየካቲት 02/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለአገልግሎት ጥቅም ላይ ስለማይውል ግብር ከፋዮች አዲሱን ባለባር ኮድ እንዲያሳትሙ ብለዋል።

ቢሮውና በስሩ ያሉት የዞንና የወረዳ ገቢ መዋቅሮች በተለያዩ ሁነቶች እንዲሁም በለያዩ መገናኛ አውታሮች ለግብር ከፋዮች የግንዛቤና የቅስቀሳ ስራ ሲሰራ መቆየቱን አብራርተዋል።

በመሆኑም ግብር ከፋዩ ቀሪ ቀናት እየተጠናቀቁ በመሆናቸው መዘናጋት እንደሌለበት አሳስበው በክልሉ 6,291 ደረሠኝ ተጠቃሚ ግብር ከፋዮች ሲኖሩ እስካሁን 841 ያህል ደረሠኝ ተጠቃሚ ግብር ከፋይ ብቻ አሳውቀው ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፈቃድ የወሰዱ መሆኑን አቶ ወንዱ ታደሰ ገልፀዋል።

ስለሆነም በቀሪዎቹ አምስት ቀናት ግብር ከፋዩ አዲሱን ባርኮድ የተተከለበትን ደረሠኝ ማሳተም እንዳለበት የገለፁት ምክትል ቢሮ ኃላፊው ከየተካቲት 02/2017 ዓ.ም በኋላ ነባሩን ደረሠኝ መጠቀም አስተዳደራዊና ህጋዊ ተጠያቂነት የሚያስከትል መሆኑን ገልፀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *