በክልሉ ያለውን ሰላምና ፀጥታ በዘላቂነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ስራዎችን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ ተናገሩ

Spread the love

ርዕሰ መስተዳድሩ በምዕራብ ኦሞ ዞን ስላለው ወቅታዊ የሠላምና ፀጥታ ጉዳይ ላይ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና ጋር የውይይት መድረክ በሚዛን አማን ከተማ አካሂደዋል።

በመድረኩ ላይ በምዕራብ ኦሞ ዞን ከሚገኙ ከአራት ወረዳዎች የተውጣጡ አመራሮችና የሀገር ሽማግሌዎች ተሳትፈዋል።

በምዕራብ ኦሞ ዞን የአርብቶ አደር አካባቢዎች አልፎ አልፎ የሚከሰተውን የእርስ በርስ ግጭት በዘላቂነት ለመፍታት በየደረጃው የሚገኙ አካላት በቅንጅት መስራት አለባቸው ብለዋል።

አካባቢው ከሚያጋጥሙ ችግር ወጥቶ ወደልማት ፊቱን እንዲያዞር ለማድረግ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች የሚጠበቅባቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

በቀጣይ አካባቢውን ሠላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ የተደራጀ የፀጥታ መዋቅር በማደራጀት በኩል በየደረጃው ያለ መዋቅር ሃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በምዕራብ ኦሞ ዞን እየተከሰቱ ስላሉት የፀጥታ ችግሮች ለበርካታ ችግሮች እየዳረጉ በመሆናቸው የተጠናከረ ስራ መሰራት እንዳለበት አንስተዋል ።

በአርብቶ አደሩ አካባቢ በተደጋጋሚ የሚታየው የከብቶች ዝርፊያና ተያያዥ ግጭቶች የሰላም እጦት ዋነኛ መንስኤ በመሆናቸው ይህም ለሕይወት መጥፋትና ለንብረት መውደም እየዳረጉ ስለሆነ ማህበረሰብን ያሳተፈ ወንጀል መከላከል በመሥራት ችግሩን በዘላቂነት መፍታት እንዳለበት በውይይቱ ተነስቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *