የአቅም ደካሞች ቤት ግንባታ ማስጀመሪያ ፕሮግራም በክልሉ ከሚከናወኑ ሰው ተኮር አገልግሎት አንዱ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለጸ
የክልሉ ትምህርት ቢሮ አመራሮችና ተጠሪ ተቋማት በጋራ በመሆን በቦንጋ ከተማ 180 ሺህ በሚሆን የገንዘብ ወጪ የሚሰራ የአቅም ደካሞች ቤት ግንባታ ስራ አስጀምሯል፡፡ ቤት ግንባታ ፕሮግራሙን ያስጀመሩት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ የ2016 በጀት ዓመት የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በጎነት ለኢትዮጵያ…
