በሰው መነገድና ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀሎችን ለመከላከል በጋራ እየተሰራ ነው
በሰው መነገድና ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀሎችን ለመከላከል በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ። ብሔራዊና ክልላዊ የፍልሰት ትብብር ጥምረት የ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ ክንውንና ቀጣይ ትኩረት ላይ የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ በአዳማ በመካሄድ ላይ ይገኛል። የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በላይሁን ይርጋ በመድረኩ ላይ እንደገለፁት መደበኛ ባልሆነ መንገድ ከሀገር የሚወጡ ዜጎች ለተለያየ ሰብዓዊ መብት…
