




ይህም የተገለጸው በቱሪዝም ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የተመራ “ቱር ኢትዮጵያ” ልዑክ በካፋ ዞን የቡና መገኛ የሆነቹን ዴቻ ወረዳ ማኪራ በመሄድ በጎበኙበት ወቅት ነው።
ኢትዮጵያ ያላትን የቱሪስት መስህቦችን በመለየት፣ ለማልማትና ለማስተዋወቅ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን በቱሪዝም ሚኒስቴር የመረጃ ሲኒየር ባለሙያ አቶ አለማየሁ ወርቀዣ ገልጸዋል
ለቱሪዝም ዘርፉ በተሰጠው ትኩረት የገቢ ምንጭ እና የስራ ዕድል ፈጠራ እንዲሆን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል ።
በሀገራችን የቡና መስመር ተብሎ ከተለዩት አካባቢዎች አንዱ ካፋ መሆኑን ጠቅሰው በዞኑ ያለው የቡና ሀብት የቱሪስት መስህብ እንደሆነም አስረድተዋል ።
በዞኑ ያለው እምቅ የተፈጥሮና ታሪካዊ ሀብቶችና ጸጋዎች በዓለም በማስተዋወቅ የገቢ ምንጭና የስራ ዕድል ፈጠራ መስክ ማድረግ ያስፈልጋልም ብለዋል።
ከሉዑኩ አንዱ የሆኑት የቱሪዝም ጋዜጠኛ አቶ ዘርሁን ግርማ በበኩላቸው ኢትዮጵያን ምድረ ቀደምት ሆና እንድትታወቅ ካደረጋት ሀብቶች አንዱ ቡና መሆኑን ጠቅሰዋል ።
ደቡብ ምዕራብ እንዲሁም ካፋ የቡና ቱሪዝም ለማሳደግ ከፍተኛ የምርታማነት አቅም አለው ያሉት ጋዜኛው ያለውን አቅም በማልማትና በማስተዋወቅ ተጠቃሚ መሆን ያስፈልጋል ብለዋል።
በካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ማኪራ ቀበሌ ቡኒ መንደር የሚገኘውን የተፈጥሮ ጫካ ቡና በማየታቸው ዕድለኛ መሆናቸውን አቶ ዘርሁን ገልጸዋል።
የቡናን ታሪክ ማንም እንደማይቀይረው የተናገሩት ጋዜጠኛና ጎብኚው ታሪክ በራሱ አንድ የቱሪስት መዳረሻ መሆኑን ጠቅሰዋል
ካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ማኪራ ቀበሌ ቡኒ መንደር ለዓለም ቡናን ያበረከተች ምድር መሆኗን በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የዴቻ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወንዱ አደመ ተናግረዋል ።
አካባቢው ፍፁም ሠላማዊ፣ እንግዳ ተቀባይና ሰው አክባሪ ማህበረሰብ ያለበትና ተፈጥሮና ሰው ተስማምተው የሚኖሩበት መሆኑን ተናግረዋል።
ጎብኚዎች የተመለከቷቸውን ተፈጥሯዊና ሰው-ሰራሽ መስህቦች ለዓለም በማስተዋወቅ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።
በዞኑ ከ1 መቶ 38 በላይ የቱሪስት መዳረሻዎችን በመለየት የማልማትና የመንከባከብ ሥራ መጀመሩን የካፋ ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ታረኳ ታከለ አመላክተዋል።
የተፈጥሮ ጫካ ቡና ከማኪራ ቡኒ ጀምሮ በዞኑ አብዛኛው አካባቢዎች ላይ እንዳለም ተናግረው ይሄውም የሰው እጅ ንኪኪ ያልታከበት መሆኑንም ጠቅሰዋል ።
በቱር ኢትዮጵያ ጎብኝት ላይ የቱሪዝም ሚኒስቴር ባለሙያዎች ፣አስጎብኚ ድርጅቶች ፣የቱሪዝም ማህበራት ተወካዮችና በቱሪዝም ዘርፍ የሚሰሩ ጋዜጠኞች መሳተፋቸው ተገልጿል ሲል የዞኑ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
