


የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ በታርጫ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
ሁለተኛ ቀኑን በያዘው የክልሉ ምክር ቤት ወደ ከተማ የተካለሉ ቀበሌዎች ሞሽን መርምሮ ያጸደቀ ሲሆን ቀበሌዎቹ በክልሉ ስር ባሉት ቤንች ሸኮ እና ሸካ ዞኖች ወደ ከተማ ቀበሌ መዋቅሮች የተካለሉት ናቸው።
በሸካ ዞን ወደ ቴፒ ከተማ ወደ ቴፕ ከተማ አስተዳድር የተካለሉት ቀበሌዎች ዝንኪ ቀበሌ ሙሉ በሙሉ፣ አዲስ አለም ቀበሌ ሙሉ በሙሉ፣አዲስ ብርሃን ቀብሌ ሙሉ በሙሉ፣ ሰላም በር ቀበሌ በከፊል፣ እና ዳሪሞ ቀበሌ በከፊል የተካለሉ ናቸው።
እንዲሁም በቤንች ሸኮ ዞን ወደ ሸኮ ከተማ አስተዳድር የተካለሉት ቀበሌዎች ሻይታ ቀበሌ ሙሉ በሙሉ፣ወሸቃ ቀበሌ ሙሉ በሙሉ፣ ቦይታ ቀበሌ በከፊል፣ ወርጉ ቀበሌ በከፊል እንዲሁም ባይነቃ ቀበሌ በከፊል ተካሏል።
በፍቅር ከበደ
