




“በሴቶች ተሳትፎ የፀናችና የበለፀገች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሀሳብ በክልሉ ብዝሃ ከተሞች ክልላዊ ማጠቃለያ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
መድረኩ ከመላ ሴቶች ጋር ሰፊ ንቅናቄ በማድረግ በብልፅግና መሪነት የሚካሄደው ሀገራዊ የለውጥ ጉዞን ሴቶች በሚገባ ተረድተው የሂደቱ ንቁ ተሳታፊና ተዋናይ እንዲሆኑ ለማስቻል ዓላማ ያደረገ ነው።
በመድረኩ “በሴቶች ተሳትፎ የፀናችና የበለፀገች ኢትዮጵያ !!” በሚል መሪ ሀሳብ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ዉይይት የሚደረግ ሲሆን የቀጣይ አቅጣጫ ይቀመጣል።
የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ስራ አስፈጻሚና የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ፕላን ቢሮ ምክትል ኃላፊ (ዶ/ር )ፈለቀች ተክለማርያም ፣የክልለ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰብለጸጋ አየለ፣ከቦንጋ ከተማ የተወጣጡ ሴቶች ክንፍ አባላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመሳተፍ ላይ ናቸው።
